loading
የሱሉልታ ከንቲባ “ቤት እናፈርሳለን አላልንም” አሉ

የሱሉልታ ከንቲባ ወይዘሮ ሮዛ ዑመር አቤቱታ በማቅረብ ላይ የሚገኙት የሱሉልታ ነዋሪዎች መኖሪያ ቤት  በሰባት ቀን ይፈርሳል የሚል ቃል አልወጣንም ብለዋል።

ከንቲባዋ  “በ7 ቀናት ማስረጃ አቅርቡ አልን እንጂ ይፈርሳል አልልንም” ይላሉ።አክለውም፦”ሁሉንም ነገር ጊዜ ወስደን፣ ከሕዝቡ ጋር ተነጋግረን፣ ተግባብተን ነው የምናደርገው” ብለዋል።አሁን ገና የማጣራት ሥራ ላይ ነን ያለነው። ይፈርሳል የተባለ ነገር የለም ” ሲሉ ነው ከንቲባዋ ለሸገር የተናገሩት።

ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው የሱሉልታ ነዋሪዎች የመኖሪያ ቤታችሁ ህገወጥ ነው ተብለን በሰባት ቀናት ውስጥ እንደሚፈርስብን ተነግሮናል በማለት ለተለያዩ አካላት አቤቱታ አቅርበው አንደነበር ይታወሳል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *