loading
ኢትሃድ አየር መንገድ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቀው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል፡፡

ኢትሃድ አየር መንገድ በታሪኩ ገጥሞት የማያውቀው ኪሳራ ውስጥ ገብቷል፡፡

ንብረትነቱ የተባበሩት አረብ ኤሜሬቶች የሆነው ኢትሃድ አየር መንገድ ባለፈው የፈረንጆቹ ዓመት 1.8 ቢሊዮን ዶላር ኪሳራ እንዳጋጠመው ይፋ አድርጓል፡፡

ይህም ጠቅላላ ገቢው በ2017 ከነበረው ጋር ሲነፃፀር በ2.4 በመቶ ዝቅ ማለቱን ያሳያል ነው የተባለው፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው አየር መንገዱ በ2017 ጠቅላላ ዓመታዊ ገቢው 6 ቢሊዮን ዶላር የነበረ ሲሆን በ2018 ወደ 5.6 ዶላር ቢሊዮን ገደማ  ወርዷል፡፡

የኪሳራው ምክንያት የመንገደኞች መቀነስ ሲሆን እንደ አውሮፓዊያኑ አቆጣጠር በ2017 18.6 ሚሊዮን መንገደኞችን ያጓጓዘው አየር መንገዱ በቀጣዩ ዓመት ግን የመንገደኞች ቁጥር ወደ 17 .8 ሚሊዮን ዝቅ ማለቱን  ተናግሯል፡፡

ከዚህ በተጨማሪም ኢትሃድ አየር መንገድ ከጀርመኑ ኤር በርሊን ጋር በገባው የፍርድ ቤት ክርክር ከ2 ቢሊዮን ዶላር በላይ የካሳ ክፍያ  ይጠብቀዋል እየተባለ ነው፡፡

 

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *