loading
ሩሲያ የክሬሚያን አምስተኛ ዓመት እያከበረች ነው፡፡

ሩሲያ የክሬሚያን አምስተኛ ዓመት እያከበረች ነው፡፡

ሞስኮ ክሬሜያን ወደ ራሷ ግዛት የቀላቀለችበትን ቀን ለሶስት ቀናት በሚቆይ ደማቅ  ስነስርዓት እያከበረችው ነው፡፡

ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን በስፍራው ተገኝተው ለግዛቲቱ የተገነባውን የሀይል ማመንጫ ጣቢያ መርቀው ከፍተዋል፡፡

ሲ ጂ ቲ ኤን እንደዘገበው በሩሲያ ድርጊት ቅር የተሰኘው የአውሮፓ ህብረት አስቸኳይ ስብሰባ ጠርቶ በሞስኮ ላይ ጫና ለመፍጠር የሚያሰችል ውይይት አድርጓል፡፡

የህብረቱ የውጭ ጉዳዮች ሀላፊ ፍሬዴሪካ ሞጎሪኒ ክሬሚያን በሀይል ከዩክሬን ለነጠቀችው ሩሲያ እውቅና የመንፈግ ፖሊሲያችን ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል፡፡

አሜሪካ፣ ካናዳና የአውሮፓ ህብረትም ባለፈው ሳምንት በሩሲያ ከደርዘን በላይ በሆኑ ባለ ስልጣናት እና የቢዝነስ ተቋማት ላይ አዲስ ማእቀብ ጥለዋል፡፡

ሀገራቱ አሁንም ክሬሚያ ለዩክሬን መመለስ አለባት የሚል አቋም ያላቸው ሲሆን ማእቀቡም በፑቲን አስተዳደር ላይ ጫና ለመፍጠር ያለመ ነው ተብሏል፡፡

የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል አቀባይ ማሪያ ዛካሮቫ ግን የክሬሚያ ነዋሪዎች ከሩሲያ ጋር የተቀላቀሉት በፍላጎታቸው ስለሆነ ያለቀለት ጉዳይ ነው፤ ከእንግዲህ የሚለወጥ ነገር የለም ብለዋል፡፡

በዓሉ በሁለቱ ሀገራት በኩል የተለያየ ገፅታን ፈጥሯል፡፡ ዩክሬናዊያን ከወዲያ ሩሲያን እየረገሙ ብስጭታቸውን ይገልፀሉ፡፡

ሩሲያዊያ ደግሞ ከወዲህ በቀድሞዋ ሶቬት ህብረት ዘመን ይዘፈን የነበረውን ዋልትዘ ኦፍ ሴባስቶፖል የተሰኘውን ተወዳጂ ዜማ እያቀነቀኑ በዳንስ ወገባቸውን ያውረገርጋሉ፡፡

መንገሻ ዓለሙ

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *