loading
ኢትዮጵያ ለቶጎና ቻድ በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ኢትዮጵያ ለቶጎና ቻድ በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ ልታደርግ ነው

ኢትዮጵያ በቅርቡ ለቶጎና ቻድ በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ ልታደርግ መሆኑን የኢትዮጵያ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን አስታወቀ።

የባለስልጣኑ ዋና ዳሬክተር ኮሌኔል ወሰንየለህ እንዳሉት ድርጅቱ የኢትዮጲያ አየር መንገድ አገልግሎት ጥራትን ከማስጠበቅ ባሻገር ለተለያዩ ሀገራት በሲቪል አቪየሽን ዘርፍ ድጋፍ እያደረገ ነው።

በዚህ መሰረትም ባለፉት ሁለት ዓመታት ውስጥ ለጅቡቲ፣ሱዳን፣ ማላዊ እና ለሌሎች ጎረቤት ሀገራት በአየር ትራፊክ ቁጥጥር ላይ ያተኮረ ድጋፍ መደረጉን ተደርጓል ብለዋል።

በተለይም ማላዊ በአለም አቀፍ ሲቪል አቪየሽን ባለስልጣን በቀይ መስመር ከተመዘገበችበት ዝርዝር ውስጥ በኢትዮጵያ በተደረገላት የአቪየሽን ሙያ ድጋፍ ልትወጣ መቻሏን ዳይሬክተሩ አብራርተዋል ።

በአጠቃላይ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ድርሻ በገዛባቸው ሀገራት ሁሉ የሀገሪቱን የሲቪል አቪየሽን ተደራሽነት ለማጠናከር የሚያደርገው ድጋፍ ተጠናክሮ የሚቀጥል መሆኑንም ጠቁመዋል።

ይህም የአየር መንገዱን ደህነንት ከማስጠበቅ ባለፈ ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚኖረውን ሁለንተናዊ ግንኙነት ለማጠናከር የሚያስችል መሆኑን ኮሎኔል ወሰንየለህ ተናግረዋል።ዘገባው የፋና ነው።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *