loading
 ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያዩ

 

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከኳታር ጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያዩ፡፡

በኳታር ይፋ የስራ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ ከሀገሪቱ ጋር ያለውን የሁለትዮሽ ግንኙነት ማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ  ከጠቅላይ ሚኒስትር አብዱላሂ ቢን ናስር ቢን ካሊፋ አል ታሃኒ ጋር ተወያይተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሮቹ ኢትዮጵያ በአፍሪካ አህጉር ካላት ትልቅ ሚና አንፃር በበርካታ ጉዳዮች ላይ ትብብራቸውን ለማጠናከር ውይይት አድርገዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ከጉብኝታቸው ጎን ለጎን እስላሚክ አርት ቤተ መዘክርን ጎብኝተዋል፡፡

በቤተ መዘክሩ የሚገኙ የብረት፣ እንጨት፣ ሴራሚክ፣ ጨርቃጨርቅ እና የሌሎችን እስላማዊ የጥበብ ውጤቶችን ጎብኝተዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በጉብኝታቸው ወቅት በቤተ መዘክሩ ዋና ስራ አስፈፃሚ የሙዚዬሙን አጠቃላይ ሁኔታ የሚያሳይ ስጦታ እንደተበረከተላቸው ነው የተነገረው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *