loading
በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የካንሰር ህመሞችን ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በኢትዮጵያ እና በአጋር አካላት መካከል ተፈረመ

በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የካንሰር ህመሞችን ለማከምና ለመከላከል የሚያስችል የሶስትዮሽ የመግባቢያ ሰነድ በኢትዮጵያ እና በአጋር አካላት መካከል ተፈረመ፡፡

ስመምነቱ በህፃናት ላይ የሚያጋጥሙ የኦንኮሎጂና ኬማቶሎጂ የካንሰር አይነቶችን ለማከም፣ ለመከላከልና የአቅም ማጎልበቻ ስልጠናዎችን ለህክምና ባለሙያዎች መስጠት የሚያስችል ነው ተብሏል፡፡

 

ስምምነቱን የተፈራረሙት የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ዶ/ር ሊያ ከበደ፣ የጥቁር አንበሳ ሆስፒታል ስራ አስኪያጅ ዶ/ር ይርጉ ገ/ህይወት እንዲሁም በአይስላንድ  የፕሮጀክቱ ዋና ዳይሬክተር የሆኑት ጁሊ ብሮስ ናቸው፡፡

እንደ ሚኒስትር ዴኤታዋ ገለጻ በአለም ላይ ህፃናትን ከሚያጋጥማቸው የካንሰር ህመም ውስጥ ከ90 በመቶ በላይ የሚሆነው የሚድን ሲሆን  በሀገራችን ያለው የግብዓት እጥረትና የእውቀት ክህሎት ክፍተትም አንዱ ተግዳሮት ነው። ፕሮጀክቱ  በካንሰር የተያዙ ህፃናት ከማከም ጋር በተያያዘ ጥሩ ውጤት እንደሚመዘገብ እምነታቸውን መሆኑንም ሚኒስትር ዲኤታዋ  ገልጸዋል፡፡

በአሁኑ ወቅት 70 ሺህ የሚደርሱ የካንሰር ታካሚዎች ሲኖሩ ከነዚህ ውስጥ ወደ 12 ሺህ የሚደርሱት ህፃናት መሆናቸውን የጠቀሱት ሚኒስተር ዲኤታዋ ይህ ስምምነት በተለይ እነዚህን ህፃናት ለማከምና ለመታደግ ትልቅ አስተዋጽኦ ይኖረዋል ማለታቸውን ከሚኒስቴሩ የተገኘው መረጃ  ያመለክታል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *