loading
የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ ተሸጋግሯል።

በ17ኛ ሳምንት በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ዕሁድ ኢትዮጵያ ቡና በአዲስ አበባ ስታዲየም ከደደቢት ጋር ሊያካሄደው የነበረው ጨዋታ ወደ ሌላ ጊዜ መተላለፉ ተነግሯል፡፡

የክለቡ ጨዋታ ለሌላ ጊዜ የተላለፈው አራት ተጫዋቾቹን ማለትም አማኑኤል ዮሐንስ፣ አቡበከር ናስር፣ ሐሰን ሻባኒ እና ክሪዚስቶም ንታምቢ በብሔራዊ ቡድን ጥሪ ምክንያት ከቡድኑ ውጭ በመሆናቸው ወደ ሌላ ቀን እንዲራዘምለት በጠየቀው መሰረት፤ ፌዴሬሽኑ ጨዋታውን ወደ ሌላ ጊዜ ማስተላለፉን ሶከር ኢትዮጵያ አስታውቃለች፡፡

በተያያዘ መረጃ ኢትዮጵያ ቡና የጨዋታውን መራዘም ተከትሎ ከሱዳኑ አል ሜሪክ ጋር የወዳጅነት ጨዋታ ነገ ረፋድ በ4:00 ሰዓት በያያ ቪሌጅ ሜዳ ያደርጋል ተብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *