loading
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መቐለ ከተከታታይ ድል በኋላ ነጥብ ጥሏል

የ17ኛ ሳምንት መርሃግብር የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ከባለፈው ዓርብ ጀምሮ እየተካሄዱ ነው፡፡

ዓርብ ዕለት ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ስታዲም ላይ አዳማን በጌታነህ ከበደ ብቸኛ ግብ 1 ለ 0 ረትቷል፡፡

ቅዳሜ በስዩም ከበደ የሚመራው መከላከያ በባለፈው ዓመት ሻምፒዮን ጅማ አባ ጅፋር 4 ለ 0 ተሸንፏል፤ ወደ ድል እየተመለሰ የሚገኘው ደቡብ ፖሊስ ድሬዳዋ ከነማን በመሸነፍ ከወራጅ ቀጠና ወጥቷል፡፡

በትናንትናው ዕለት ደግሞ ሶስት ጨዋታዎች ቀጥለው ሲደረጉ፤ የሊጉ መሪ መቐለ 70 እንደርታ ትግራይ ስታዲየም ላይ ከወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ ጋር 1 ለ 1 አቻ ተለያይቶ፤ ከአስር ጨዋታዎች ድል በኋላ ነጥብ ጥሏል፡፡

ወደ ሀዋሳ ያቀናው ፋሲል ከነማ 2 ለ 2 አቻ ውጤት ተለያይቶ ተመልሷል፡፡

ሽረ ላይ ስሑል ሽረ ባህር ዳር ከነማን 1 ለ 0 በመርታት ያልተጠበቀ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

ዛሬ በአዲስ አበባ ስታዲየም አንድ ጨዋታ የሚደረግ ሲሆን በሁለቱ የደቡብ ክለቦች ሲዳማ ቡና እና ወላይታ ድቻ መካከል ይካሄዳል፡፡

በሳምንቱ መርሀግብር ተይዞለት የነበረው የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት መካከል ሊካሄድ የነበረው ጨዋታ፤ ቡና አራት ተጫዋቾችን ለብሔራዊ ቡድኖች በማስመረጡ ለሌላ ጊዜ ተላልፏል፡፡

የሊጉን የደረጃ ሰንጠራዥ መቐለ 70 እንደርታ በ39 ነጥብ ይመረዋል፤ ሲዳማ ቡና በ30 ሲከተል ፤ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ፋሲል ከነማ በተመሳሳይ 29 ነጥቦች ሶስተኛ እና አራተኛ ደረጃ ላይ ተቀመጠዋል፡፡

ወላይታ ድቻ፣ ስሑል ሽረ እና ደደቢት አሁንም ወራጅ ቀጠና ውስጥ ይገኛሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *