loading
ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

ኢትዮጵያና የአውሮፓ ህብረት ግንኙነታቸውን ለማጠናከር ተስማሙ

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ በኢትዮጵያ የአውሮፓ ህብረት አምባሳደር ጆን ቦርግስተን የተመራ የህብረቱን የልዑካን ቡድን በጽህፈትቤታቸው ተቀብለው አነጋግረዋል።

በዚህም በህብረቱና በኢትዮጵያ መካከል ስላለው ግንኙነት፣ አህጉራዊና ቀጣናዊ ጉዳዮች በተለይም በሰላምና ጸጥታ፣ ፍልሰት፣ የአየር ንብረት ለውጥ እና የመልካም አስተዳደር ረገድ ሁለቱ አገራት በጋራ መስራት በሚችሉባቸው ጉዳዮች ዙሪያ ተወያይተዋል።

ሁለቱ አጋር አካላት የንግድ፣ የቢዝነስና የኢንቨስትመንት ትስስርን ማጠናከር ጠቃሚ መሆኑን ወ/ሮ ሂሩት በዚሁ ወቅት ገልጸዋል።

ኢትዮጵያ በቀጣናው በተላይም በሶማሊያና ደቡብ ሱዳን ዘላቂ ሰላም አንዲሰፍን ገንቢ ሚናዋን ከአውሮፓ ህብረት ጋር ተባብራ እንደምትቀጥልም ተናግረዋል ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይ ሚኒስቴር ገልጿል።

አምባሳደር ጆን ቦርግስተን በበኩላቸው የአውሮፓ ህብረት ኢትዮጵያን በአፍሪካ እንደ ቀዳሚ አጋር እንደሚመለከት ገልጸው ግንኙነቱ የበለጠ እንዲጠናከር ፍላጎታቸው መሆኑን ገልጸዋል።

ህብረቱ እንደ ሰላምና ጸጥታ፣ ፍልሰት፣ የአየር ንብረት ለውጥና መሰል ጉዳዮች ዙሪያ ከኢትዮጵያ ጋር ተባብሮ መስራቱን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *