loading
የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ  ቤት ቅርስ ስለሆነ እንዳይፈርስ ከቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር ተስማምቼ ነበር አለ፡

የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ  ቤት ቅርስ ስለሆነ እንዳይፈርስ ከቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር ተስማምቼ ነበር አለ፡፡

ቤቱ እንዴት እንደፈረሰም እያጣራሁ ነዉ ብሏል

የአ.አ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ (የልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ የልጅ ልጅ) መኖሪያ ቤት የነበረው እና በባህል እና ቱሪዝም በቅርስነት የተመዘገበው ቤት ቅርስ ስለሆነ እንዳይፈርስ ከቤቶች ኮርፖሬሽን ጋር ተስማምተን ነበር ብሏል፡፡

በሌላ በኩል ዛሬ ከረፋዱ አምስት ሰዓት አካባቢ በፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ታዘን ነው በሚል በቡልዶዝር መኪና ይህን በቅርስነት የተመዘገበ ቤት አፍርሰዋል፡፡

በአ.አ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ  የቋሚ ቅረስ ጥበቃ እና ምዝገባ ባለሞያ የሆኑት ወ/ሮ ዘውድነሽ መንገሻ ለአርትስ ቲቪ እንደነገሩን የአ.አ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮ የደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ (የልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ የልጅ ልጅ) መኖሪያ ቤት የነበረው ቤት የፌደራል ቤቶች ኮርፖሬሽን ቤቱን አፍርሶ የመኖሪያ አፓርትመንት ለመገንባት የአፓርትመንት ዲዛይን አሠርቶ ይፋ አድርጓል፡፡

ዲዛይኑን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ የየካ ክፍለ ከተማ እና የባህል እና ቱሪዝም ቢሮ ቤቱ በቅርስነት የተመዘገበ መሆኑን ገልጸን እንዳይፈርስብን ስንል አሳስበን ነበር ብለውናል ባለሞያዋ፡፡

እንደ ወ/ሮ ዘውድነሽ ገለፃ በአካባቢው ነዋሪዎች ቤቱን ያፈረሱት ሰዎች ይዘውት የመጡት መኪና  የመለያ ቁጥር እንኳ የሌለው ነው የሚል ጥቆማ ማቅረባቸውን ተከተሎ ባህል እና ቱሪዝም ቢሮው ከቤቶች ኮርፖሬሽን መረጃውን እያጣራ ነው፡፡

ይህ በቅርስነት የተመዘገበው የደጃዝማች አምዴ አበራ ካሳ (የልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ የልጅ ልጅ) መኖሪያ ቤት ከተገነባ 90 አመት ሆኖታል፡፡

ከገነተ ኢየሱስ ቤተክርስቲያን ከፍ ብሎ፣ “የራስ ካሳ ሠፈር” (በልዑል ራስ ካሳ ኃይሉ ስም በሚጠራው ሠፈር) የአካባቢው ውበት መገለጫ ኾኖ ተለይቶ የሚታወቅ ቤት ነበር።

ቤቱ አሁን ያለበት ሁኔታ መልሶ ለመጠገን የሚሆን ከሆነ ቅርሱን እናድነዋለን ካልሆነ ግን በህግ እንጠይቃለን ብለውናል ባለሞያዋ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *