loading
በአዲስ አበባ ከተማ የመድሃኒት መደብሮች በሌሉባቸው አካባቢዎች 50 የመድሃኒት መደብሮችን ለመክፈት ጤና ሚኒስቴር እየሰራ ነው

በአዲስ አበባ ከተማ የመድሃኒት መደብሮች በሌሉባቸው አካባቢዎች 50 የመድሃኒት መደብሮችን ለመክፈት ጤና ሚኒስቴር እየሰራ ነው

የመድሃኒት አቅርቦት፣ የመግዛት አቅም መዳከም እና የአሰራር ስርዓት ችግሮች በመድሃኒት አገልግሎት ላይ የሚነሱ ተግዳሮት መሆናቸውን አቶ ያዕቆብ ሰማን በጤና ሚኒስቴር የሜዲካል አገልግሎት ዳሬክቶሬት ጄኔራል ዳሬክተር አቶ ያዕቆብ ሰማን ጠቁመዋል፡፡

እነዚህ ችግሮችን ለመቅረፍ ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት መደብሮች ዋነኛ ዘዴ መሆኑም የገለፁ ሲሆን ሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት መደብሮች የአሰራር መመሪያ በመላው አገሪቱ በሚገኙ ሆስፒታሎችና ጤና ተቋማት ተግባራዊ በሚደረግበት ወቅት መድሃኒት የመግዛት አቅማቸው ዝቅተኛ የሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎችን ተጠቃሚ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በአዲስ አበባ ከተማ የመድሃኒት አቅርቦት ዝቅተኛ ናቸው በሚባሉ እንደ ኮንደሚኒየም መደብሮች በጤና ሚኒስቴር በኩል 50 የመድሃኒት መደብሮች በዚህ አመት ተከፍተው ስራ ይጀምራሉ ተብሏል፡፡

የሞዴል የማህበረሰብ መድሃኒት መደብሮች የአሰራር መመሪያ ለሆስፒታሎች፤ ለክልሎች እና ጉዳዩ ለሚመለከታቸው አካላት በአዲስ አበባ ከተማ የግንዛቤ ማስጨበጫ ተሰጥቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *