loading
ግብጽ በ2022 የኤሌክትሪክ ድጎማ ልታቋርጥ መሆኑን ገለጸች ፡፡

ግብጽ በ2022 የኤሌክትሪክ ድጎማ ልታቋርጥ መሆኑን ገለጸች ፡፡

ግብጽ በኤሌክትሪክ ላይ የምታደርገውን ድጎማ በፈረንጆቹ 2022 ሙሉ ለሙሉ ልታቆም መሆኗን ያስታወቁት የሀገሪቱ ኤሌክረትሪክ ሚኒስትር መሐመድ ሻከር፤ ሀገሪቱ  የምትተገብረው  የኢኮኖሚ ማሻሻያ እቅድ አንዱ አካል ነው ብለዋል፡፡

ሚኒስትሩ በሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ቀርበው  በሰጡት መግለጫ የኤሌክትሪክ ክፍያ በቀጣዮቹ ሶስት ዓመታት እየጨመረ ይሄዳል ያሉ ሲሆን ፤ድጎማውን ማቋረጥ ያስፈለገው የመጠጥ ውሃ፣የኤልክትሪክና የጽዳት አገልግሎቶችን  ለህዝብ የሚሰጡ ተቋማትን  ወደ ግል የማዘዋወር እቅድ በመኖሩ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይም መንግስት ለቤት ውስጥ መጠቀሚያ ነዳጅ፣ቤንዚል እና ናፍጣ ላይ ሲያደርግ የቆየውን ድጎማ እንደሚያቆም አስታውቋል፡፡

በውሳኔው የተነሳ በከፋ ድህነት የሚኖሩ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ግብጻዊያን መሰረታዊ ፍላጎታቸውን ማሟላት የሚችሉበት ሁኔታ ውስጥ ይገባሉ ተብሏል፡፡

እንደ ሚድል ኢስት ሞኒተር ዘገባ ላለፉት አራት አመታት ፕሬዜዳንት አብዱል ፈታ አልሲሲ ወደስልጣን  ከመጡ ወዲህ የሀገሪቱ የኤሌክትሪክ ፍጆታዋ እየጨመረ መምጣቱ ተነግሯል፡፡

እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር በ2016 የሀገሪቱ መገበያያ ገንዘብ ዋጋው መውረድ ተከትሎ የተከሰተውን የዋጋ ግሽበት ለማካካስ በ2022 የሀገሪቱን የግብር ክፍያ መጠን በ131 በመቶ ላማሳደግም ታቅዷል፡፡

ይሄን የአልሲሲን ውሳኔ ተከትሎ በሺዎች የሚቆጠሩ ግብጻዊያን ተቃሙሟቸውን እየገለጹ ሲሆን ፕሬዜዳንቱ ስልጣናቸውን በፍቃዳቸው ይልቀቁ የሚሉ ድምጾች በርክተዋል ነው የተባለው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *