loading
የጤና ፖሊሲ ክለሳ መጨረሻ  ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

የጤና ፖሊሲ ክለሳ መጨረሻ  ምዕራፍ ላይ እንደሚገኝ የጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን የገለጸዉ በጤና ፖሊሲ ማሻሻያ ላይ ዉይይት በተደረገበት ወቅት ነዉ፡፡

ውይይቱን በንግግር የከፈቱት የጤና ሚኒስቴር ዴኤታ ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ የጤና ፖሊሲው እንዲሻሻል ከ2007 ዓ.ም ጀምሮ ሲሠራበት የቆየ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የመጨረሻውን ምዕራፍ የባለድርሻ አካላት ውይይት እያደረጉበት ነው ብለዋል፡፡

ቀደም ሲል አገልግሎት ላይ የቆየው የጤና ፖሊሲ ከ25 አመት በላይ የሆነው ሲሆን አሁን ካለውና ወደፊት ለሚሆነው ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ ለውጥ ጋር የተጣጣመ እንዲሆን ፖሊሲውን ማሻሻል አስፈላጊ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ሚኒስቴር ዴኤታዋ፡፡

የጤና ፖሊሲ የክለሳ መድረክ ላይ የሙያ ማህበራት፣ የዩኒቨርሲቲ ተወካዮች እና የግሉ ዘርፍ የተሳተፉ ሲሆን ከውይይቱም ፖሊሲው ይበልጥ እንዲዳብርና በቀጣይ አመታት የአገራችን የጤና ስርአት ይበልጥ በማጠናከር ጤናማ፣ምርታማና የበለጸገ ህብረተሰብ ለማየት የሚያስችል እንደሚሆን ወ/ሮ ሳህረላ አብዱላሂ ተናግረዋል፡፡

ምንጭ ፤-የጤና ሚኒስቴር

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *