EthiopiaPolitics

እኛ አጭበርባሪዎች አይደለንም አሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ

እኛ አጭበርባሪዎች አይደለንም አሉ የኦሮሚያ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ለማ መገርሳ

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት  በክልሉ ከሚገኙ ባለሃብቶች ጋር በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ውይይት ባካሄዱበት ወቅት ነው፡፡

አቶ ለማ መገርሳ  ከባለሀብቶቹ ጋር ባደረጉት ውይይት ስለ ከተማ ስርጭት (ዴሞግራፊ)፣ ስለ ደረሰባቸው የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ፣ ስለ ኢትዮጵያዊነት፣ ስለ ኦዲፒና አዴፓ ግንኙነት፣ ስለ ኦዲፒ የአመራር አንድነት እንዲሁም ሌሎች ከባለሃብቶች የተነሱ ጥያቄዎች እና ሃሳቦች ላይ ንግግር አድርገዋል፡፡

የተካሄደው ትግል ከምር እንጂ ለጊዜያዊ ማጭበርበር አይደለም ያሉት አቶ ለማ

ከባልደረቦቼ ጋር ነፍስ አስይዘንለአገሪቷና ለህዝቡ ከመታገል ውጭ የማታለል ስራ አንሰራም ብለዋል፡፡

እንደ ፕሬዝዳንቱ ገለፃ የክልሉን እና የመላው የኢትየጵያን ህዝብ ኑሮ ለማሻሻል ከሚሰራው ስራ ውጭ ስለ ዴሞግራፊ መለወጥ በተለይም በአዲስ አበባ የዲሞግራፊ ለውጥ አድርጋችኋል እየተባለ  የሚወራው የተሳሳተ አረዳድ  መሆኑን እና የተቀነባበረ የስም ማጥፋትዘመቻ እንደሆነ ገልፀዋል፡፡

አቶ ለማ በአዲስ አበባ  የተፈናቀሉ አርሶአደሮች የግፍ ግፍ ተፈፅሞባቸዋል በመሆኑም የአርሶአደሮቹ ጉዳይ የእውነት እና የፍትህ ጉዳይ እንጂ  የዴሞግራፊ ጉዳይ አይደለም ብለዋል፡፡

ጨምረውም አዲስ አበባ ላይ በዚህ መጠን  ሌላ ከተማ የሌለ እስከሚመስል ትኩረት ማድረጉ ተገቢ አይደለም ሌሎች ትልልቅ ከተሞች አሉንም ብለዋል፡፡

በወቅቱ ትኩረት የነበረው  ክልሉ በሰፊው ስለሚናጥበት የጸጥታ ችግር መሆኑን አንስተው ስለኢትዮጵያዊነት ሲናገሩም  ለሽወዳ እና ለማጭበርበር አለመሆኑን አስረግጠው ተናግረዋል፡፡

ከወራት በፊት ስለተሰጠው መግለጫም ከተሳታፊዎች ጥያቄ ቀርቦላቸው የተናገርኩትን  አንዳንድ አካላት ከአውዱ ውጭ በራሳቸው መንገድ ትርጉም ሰጥተው የፈጠሩት የተሳሳተ አረዳድ እንጂ የእኔ አስተሳሰብና አመለካከት አይደለም ብለዋል:: ኦሮሚያን መጥቀም ስህተት አድርገው የሚመለከቱ አካላት የተቀነባበረ የስም ማጥፋት ዘመቻ ነው ሲሉ ኮንነውታል፡፡

ህዝቡም የሚወጡ መረጃዎችን በማስተዋል እና በማመዛዘን መመልከት አለበት ብለዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button