loading
በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር ኢብራሂሞቪች እና ሮኒ ባስቆጠሩት ግቦች ክለቦቻቸው ድል ቀንቷቸዋል

በአሜሪካ ሜጀር ሊግ ሶከር የአምስተኛ ሳምንት መርሀግብር ግጥሚያዎች ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ በዲግኒቲ ህልዝ ስፖርትስ ፓርክ ፖርትላንድ ቲምበርስን 2 ለ 1 ባሸነፈበት ጨዋታ ስዊድናዊው የ37 ዓመት አንጋፋ አጥቂ ዝላታን ኢብራሂሞቪች በፍጹም ቅጣት ምት ሁለት ጎሎችን አስቆጥሮ ቡድኑ የ2 ለ 1 ድል እንዲቀዳጅ አስችሏል፡፡

የቀድሞው የማንችስተር ዩናይትድ አጥቂ ኢብራሂሞቪች የውድድር ዓመቱ መክፈቻ ጨዋታ ጀምሮ በጉዳት ምክንያት ለቡድኑ ግላጋሎት ያልሰጠ ሲሆን ወደ ጨዋታ በተመለሰበት ዕለት ሁለት ግቦችን ማስቆጠሩ ውዳሴ እንዲጎርፍለት ሁኗል፡፡ ጀረሚ ኢቦቢሴ የፖርትላንድን አንድ ግብ ከመረብ አዋህዷል፡፡

ሎስ አንጀለስ ጋላክሲ ካደረጋቸው አራት ግጥሚያዎች በሶስቱ ድል አሳክቷል፡፡

እንግሊዛዊው ዋይኒ ሮኒ ሚገንበት ዲሲ ዩናይትድ ከሜዳው ውጭ በኦርላንዶ ሲቲ ላይ የ2 ለ 1 ውጤት ሲያገኝ ሮኒ ከቅጣት ምት ያቆጠራት ግሩም ግብ ለቡድኑ ድል ትልቅ ሚና ተጫውቷል፡፡

ስቲቭ ቢርናቡም ሌላኛዋን የክለቡን ግብ ከመረብ አሰቀድሞ ከገናኝቷል፡፡

በዚህም ዲ.ሲ ዩናይትድ በዞኑ ያለውን የደረጃ ሰንጠራዥ ከአራት ጨዋታዎች 10 ነጥቦችን ሰብስቦ አናት ላይ መቀመጥ ችሏል፡፡ በአጠቃላይ ደግሞ ሁለተኛ ደረጃ ላይ ተገኘቷል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *