loading
የ33ኛ ሳምንት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ይካሄዳሉ

የሊጉ የ32ኛ ሳምንት ግጥሚያዎች የመጨረሻ ጨዋታ ትናንት ምሽት በአርሰናል እና ኒውካስትል ዩናይትድ መካከል ኤመሬትስ ላይ ተካሂዷል፡፡

በሙሉ ጨዋታው መድፈኞቹ ደረጃቸውን ወደ ሶስት ከፍ ያደረጉበት የ2 ለ 0 ድል ውጤት አስመዝግበዋል፡፡

የዩናይ ኤመሪ ልጆች በምሽቱ ሶስት ነጥብ እንዲያሳኩ ያደረጉ የድል ጎሎችን ዌልሳዊው አሮን ራምሴ እና ፈረንሳያዊው አጥቂ አሌክሳንደር ናቸው፡፡

ቡድኑ በ63 ነጥብ ደረጃውን ወደ ሶስተኛ ከፍ በማድረግ የጎረቤቱን ቶተንሃም ሆትስፐር ቦታ ቀምቷል፡፡

የመድፈኞቹ ድል በኤመሬትስ አስረኛ የተመዘገበ ተከታታይ  ድል ሁኗል፡፡

በየካቲት 2019 መጀመሪያ አርሰናል ከጎረቤቱ እና ተቀናቃኙ ቶተንሃም ሆተስፐርስ የነበራቸው የነጥብ ልዩነት 10 የነበር ሲሆን አሁን ግን ከሁለት ወር በኋላ ሊጉ ሊጠናቀቅ የስድስት እና ሰባት ሳምንታት ዕድሜ እየቀረው ከቶተንሃም እና ማንችስተር ዩናይትድ    በሁለት ነጥብ ልቆ ሶስተኛ ደረጃን ተቆናጥጧል፡፡ 

ዛሬ እና ነገ ምሽት ደግሞ የ33ኛ ሳምንት አምስት ፍልሚያዎች ሲደረጉ በዛሬው ምሽት ሁለት ግጥሚያዎች ብቻ ይከናወናሉ፡፡

የላንክሻየሩ ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ምዕራብ ሚድላንድስ ተጉዞ በሞሊኒክስ ስታዲየም ከወልቨረርሃምፕተን ጋር ይፋጠጣል፡፡

ከ18 ቀናት በፊት ሁለቱ ቡድኖች በኤመሬትስ ኤፍ ኤ ዋንጫ ተገናኝተው በኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የሚመራው ቡድን የሶልሻዬርን ቡድን ከውድድር ማሰናበቱ ይታወሳል፡፡

በቀያይ ሰይጣኖቹ በኩል አሌክሲስ ሳንቼዝ፣ አንቶኒዮ ቫሌንሲያ፣ ኤሪክ ቤይሊ እና ማቲዎ ዳርሚያን ከጨዋታው ውጭ ናቸው፡፡

ጨዋታው ምሽት 3፡45 ሲል ይጀመራል ፡፡

ሌላኛው በተመሳሳይ ሰዓት የሚደረገው ጨዋታ ደግሞ በዋትፎርድ እና ፉልሃም መካከል በቪካሬጅ ሮድ ስታዲየም ይከናወናል፡፡

ፕሪምየር ሊጉን ሊቨርፑል በ79 ነጥቦች ሲመራ አንድ ተስተካካይ ጨዋታ ያለው ማንችስተር ሲቲ በ77 ነጥብ ሁለተኛ ደረጃ ሁኖ ይከተለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *