loading
የአርመኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው

የአርመኒያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ኢትዮጵያን ሊጎበኙ ነው
የአርመኒያ ሪፐብሊክ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዞህራብ ማታካንያን ለሁለት ቀናት ይፋዊ የስራ ጉብኝት ነገ መጋቢት 25 ቀን 2011 ዓ.ም አዲስ አበባ ይገባሉ።

በኢትዮጵያ ቆይታቸው ከፕሬዝዳንት ሳህለወርቅ ዘውዴ እና ከውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ  ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ጋር በሁለትዮሽ ጉዳዮች ዙሪያ ይወያያሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ ጉብኝት ሁለቱ አገራት በትምህርት፣ ቱሪዝም፣ ባህል፣ በአቅም ግንባታ ዘርፎች ያላቸውን ትብብር እንደሚያጠናክረው ይጠበቃል።

ኢትዮጵያና አርመኒያ በርካታ ዘመናትን የተሻገረ የህዝብ ለህዝብ ግንኙነት ያላቸው ሲሆን በዘማናዊት ኢትዮጵያ ግንባታ ሂደት ውስጥ አርመኒያ ጉልህ ድርሻ አላት።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *