loading
ማንችስተር ዩናይትድ ሽንፈት ሲገጥመው፤ ፉልሃም ከፕሪምየር ሊጉ መውረዱ ተረጋግጧል::

የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ የ33ኛ ሳምንት መርሀግብር ሁለት ጨዋታዎች ተከናውነዋል፡፡

በኦሌ ጉናር ሶልሻዬር የሚመራው ማንችስተር ዩናይትድ ወደ ዌስት ሚድላንድስ አምርቶ በሞሊኒክስ ስታዲየም ከወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ ግጥሚያውን አድርጎ ከመሪነት ተነስቶ ሽንፈት አስተናግዷል፡፡

ቀያይ ሰይጣኖቹ በስኮት ማክቶሚናይ ግብ ቀዳሚ የመሆን ዕድል ቢያገኙም ፤ የኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ ቡድን በዲዬጎ ጆታ ጎል አቻ ሲሆን የማሸነፊያዋን ጎል ደግሞ ክሪስ ስሞሊንግ በራሱ መረብ ላይ ለወልቭስ አስቆጥሯል፡፡

ዩናይትድ በደረጃ ሰኝጠራዡ አራቱ ቡድኖች ዝርዝር ውስጥ ለማጠናቀቅ የሚያደርገው ጥረት ላይ ወደ ኋላ እያፈገፈገ ያለ ይመስላል፡፡

በሌላ ጨዋታ ዋትፎርድ ቪካሬጅ ስታዲየም ላይ ፉልሃምን ገጥሞ 4 ለ 1 ሲረታ፤ የለንደኑ ቡድን ፉልሃም ሶስት አሰልጣኞችን መቀያየር ቢችልም በመጣበት ዓመት ወደ ታችኛው የውድድር መድረክ (ሻምፒዮንሽፕ) ወርዷል፡፡

ዛሬ ምሽት ሶስት ግጥሚያዎች የሚከናወኑ ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *