loading
የኢትዮጵያ ኦሊምፒክ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ማጣሪያውን ዛሬ ይጀምራል፡፡

በ2020 ለሚካሄደው የቶኪዮ ኦሊምፒክ የሴቶች እግር ኳስ ውድድር ለመካፈል የአፍሪካ ዞን የመጀመሪያ ዙር የማጣሪያ ጨዋታዎች መካሄድ ዛሬ ይጀመራል፡፡

የኢትዮጵያ ሴቶች ኦሊምፒክ ቡድን የመጀመሪያ ዙር ቀዳሚ ጨዋታውን በሜዳው በአዲስ አበባ ስታዲየም ከዩጋንዳ አቻው ጋር ቀን 10፡00 ላይ የሚያከናውን ይሆናል፡፡

በአሰልጣኝ ሰላም ዘራይ የሚመራው ብሔራዊ ቡድኑ በትናትናው ዕለት የመጨረሻ ልምምዱን ሰርቷል፡፡

የ25 ተጫዋቾች ስብስብ ያለው ብሔራዊ ቡድን በሙሉ ጤንነት ላይ እንደሚገኝ ተነግሯል፡፡

በትናንትናው ዕለት ማለዳ ወደ አዲስ አበባ የገባው የዩጋንዳ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከሶከር ኢትዮጵያ በተገኘው መረጃ መሰረት ትናንት አመሻሽ 11:00 በአዲስ አበባ ስታዲየም ሊያደርጉት የነበረው ልምምድ በጣለው ዝናብ ምክንያት ሳይከናወን ቀርቷል፡፡

የዩጋንዳ ቡድን 28 የቡድን አባላትን በመያዝ ቤስት ዌስተርን ሆቴል እንዳረፈ ተነግሯል፡፡

ዛሬ የሚደረገው የማጣሪያ ጨዋታ በግብፃውያን አርቢትሮች እንደሚመራ ተጠቁሟል፡፡

የመልሱ ጨዋታ ከሦስት ቀናት በኋላ በዮጋንዳ መዲና ካምፓላ የሚከናወን ሲሆን አጠቃላይ አሸናፊ የሚሆነው ብሔራዊ ቡድን በሁለተኛው ዙር ከካሜሮን ጋር እንደሚገናኝ ታውቋል፡፡

በጨዋታው የሚገኘው የተመልካች ገቢ ለቀድሞው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ተጫዋች ሞገስ ታደሰ ህክምና ይውላል ተብሏል፡፡

በሌሎች የአፍሪካ ሀገራት የማጣሪያ ጨዋታዎች ኮት ዲ, ቯር አቢጃን ላይ ከ ሴራ ሊዮን፤ ጋቦን ሊብሬቪሌ ላይ ከ ኮንጎ ብራዛቪል እና ማሊ ባማኮ ላይ ከሞሮኮ ይጫወታሉ፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *