loading
በፕሪምየር ሊጉ ማንችስተር ሲቲ፣ ቶተንሃም እና ቼልሲ ድል አድርገዋል፡፡

ትናንት ምሽት ሶስት የእንግሊዝ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታዎች ተከናውነው ታላላቆቹ ቡድኖች ድል ቀንቷቸዋል፡፡

ማንችስተር ሲቲ በኢቲሃድ የዌልሱን ካርዲፍ ሲቲ አስተናግዶ፤ 2 ለ 0 በመርታት የሊጉን የደረጃ ሰኝጠራዥ መሪነት ከቀያዮቹ ተረክቧል፡፡

 ኬቨን ዲ ብሯይኔ እና ሊሮይ ሳኔ በመጀመሪያው የጨዋታ አጋማሽ የድል ጎሎችን ለዘሲቲዚንስ ከመረብ አገናኝተዋል፡፡ ፔፕ ጓርዲዮላ እና ተጫዋቾቹ አሁንም ለአራትዮሽ ዋንጫ ሩጫው እየገሰገሱ ይገኛል፡፡

ካርዲፍ ድግሞ ከሊጉ ለመውረድ ወደ ታች ጉዞውን ገፍቶበታል፡፡

ለንደን ላይ በተገማሸረው አዲስ ስታዲየም የመጀመሪያ ጨዋታውን ያከናወነው ቶተንሃም ሆትስፐር፤ የከተማ ተቀናቃኙን ክሪስታል ፓላስ 2 ለ 0 ድል በማድረግ የሶስተኛነት ደረጃውን በ64 ነጥቦች ከመድፈኞቹ ተረክቧል፡፡

ሰን ሁንግ ሚን እና ክሪስቲያን ኢሪክሰን ስፐርሶችን ወደ ድል የመለሱ ጎሎች ከመረብ ሲያገናኙ፤ አዲስ ስታዲየማቸውን በውጤት መርቀውታል፡፡

የማውሪዚዮ ሳሪው ቼልሲ ደግሞ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ ብራይተንን ገጥሞ፤ በኦሊቪዬ ዥሩ፣ ኢዲን ሃዛርድ እና ሎፍተስ ቺክ ግቦች 3 ለ 0 አሸንፎ፤ ከአርሰናል ጋር እኩል 63 ነጥቦችን በመያዝ በግብ ክፍያ አንሶ ወደ አምስተኛ ደረጃ ላይ ከፍ ማለት ችሏል፡፡    

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *