loading
ቡና እና ደደቢት ተስተካካይ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን ዛሬ ያደርጋሉ

በ17ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ መርሀግብር መከናወን የነበረበት ፤ የኢትዮጵያ ቡና እና ደደቢት ጨዋታ ዛሬ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ በ11፡00 ላይ የሚከናወን ይሆናል፡፡

ጨዋታው በመደበኛው መርሃግብር ሊከናወን ያልቻለው፤ የቡና አራት ተጫዋቾች ለብሔራዊ ቡድን ጨዋታዎች ከቡድኑ መነጠላቸውን ተከትሎ ነው፡፡

ከአምስት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች ሽንፈት በኋላ ፤ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲን በ18ኛው ሳምንት የፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ድል በማድረግ ወደ ውጤት የተመለሰው ኢትዮጵያ ቡና ውጤት የሚቀናው ከሆነ ደረጃውን ወደ ስድስተኛ ከፍ ማለት ያስችለዋል፡፡

ወራጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘው ደደቢት ደቡብ ፖሊስ ላይ ባገኙት ድል ከሰባት ጨዋታዎች በኋላ ነጥብ ያሳኩ ሲሆን የውድድር ዓመቱን ሁለተኛ ድላቸውን አሳክተዋል፡፡

በመጀመሪያው ዙር የፕሪምየር ለጉ ጨዋታ ትግራይ ላይ ቡና ድል ማድረጉ ይታወሳል፡፡

አርቢትር ባህሩ ተካ ጨዋታውን በመሀል ዳኝነት የሚመሩት ይሆናል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *