loading
ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል የሚገኘውን ኢምባሲዋን ቀስበቀስ መዝጋት ጀምራለች፡፡

ደቡብ አፍሪካ በእስራኤል የሚገኘውን ኢምባሲዋን ቀስበቀስ መዝጋት ጀምራለች፡፡

በእስራኤል እና በደቡብ አፍሪካ መካከል ያለው ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነት በሂደት እንዲቋረጥ  ገዥው ፓርቲ አፍሪካን ናሽናል ኮንግረስ ባቀረበው ጥያቄ ነው ሀገሪቱ ከዚህ ውሳኔ ላይ የደረሰችው፡፡

ይህ የሆነበት ምክንያት ደግሞ ደቡብ አፍሪካ እስራኤል በፍልስጤም ላይ የምትፈፅመውን ግፍ ማቆም አለባት የሚል አቋም በመያዟ ነው፡፡

ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው ደቡብ አፍሪካ በመጀመሪያው ዙር ቴል አቪቭ የሚገኘውን ኢምባሲዋን ከሙሉ ጊዜ አገልግሎቱ ወደ ጉዳይ አስፈፃሚ ቢሮነት ቀይራዋለች፡፡

የደቡብ አፍሪካ የዓለም አቀፍ ግንኙነት ሚኒስትር ሊንድዊ ሲሉሉ አሁን ያለው የጉዳይ አስፈፃሚ ቢሮ የፖለቲካ፣ የዲፕሎማሲ እና የንግድ ግንኙነት የማድረግ መብት የለውም ብለዋል፡፡

ይህም ሁለቱ ሀገራት የነበራቸው ዲፕሎማሲ ግንኙነት ያለቀለት ጉዳይ መሆኑን የሚያመላክት  ነው ተብሏል፡፡

መንገ ሻዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *