loading
ኢራን የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለማቋቋም ብታስብም አቅሟ አልፈቀደላትም፡፡

ኢራን የአደጋ ጊዜ ፈንድ ለማቋቋም ብታስብም አቅሟ አልፈቀደላትም፡፡

በኢራን የደረሰው የከፋ የጎርፍ አደጋ እስካሁን 70 ሰዎችን ሲገድል ሚሊዮችን ከቀያቸው አፈናቅሏል፡፡

የኢራን መንግስት ጉዳት የደረሰባቸውን ዜጎች የእለት ደራሽ እርዳታ እንዲያገኙ ለዓለም አቀፉ ማህበረሰብ ጥሪ ቢያቀርብም የአሜሪካን ማእቀብ እየፈሩ እጃቸውን ለድጋፍ መዘርጋት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡

አለጀዚራ እንደዘገበው መንግስት የአሁኑንም ወደፊት ሊገጥም የሚችልን ችግር ለመቋቋም የሚያስችል የአደጋ ጊዜ ፈንድ ሊያቋቁም ቢያስብም እጅ አጥሮት እቅዱን ማሳካት አልተቻለውም፡፡

ነገር ግን ምንም አማራጭ ከጠፋ ከሀገሪቱ ተቀማጭ የድጎማ ሀብት እስከ 2 ቢሊዮን ዶላር በማውጣት ስራ ላይ እንዲውል ማድረጉ እንደማይቀር ተነግሯል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *