loading
ማንነትን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ እርስ በእርስ መጋጨት የለብንም አሉ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ኡመር

ማንነትን ከፖለቲካ ጋር በማያያዝ እርስ በእርስ መጋጨት የለብንም አሉ የሶማሌ ክልል ፕሬዝዳንት አቶ ሙስጠፋ መሀመድ ኡመር

ፕሬዝዳንቱ ይህን ያሉት በራስ ሆቴል በተዘጋጀው ጦቢያ ግጥምን በጃዝ ምሽት ላይ ባስተላለፉት መልዕክት ነው፡፡

በመልዕክታቸው በየአካባቢው እና በየብሄረሰቡ የየራሳቸው ስብዕና ያላቸው ሰዎች አሉ፡፡በእነዚህ ሰዎች ምክንያት ግንአንድን ብሄር በጅምላ መፈረጅ ተገቢ አይደለም ብለዋል፡፡

ሰላም እንዳይሰፍን ከሚያደርጉ ምክንያቶች መካከል ዋነኛው የመወያየት ባህል አለማዳበራችን እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

አመራር ላይ የሚመጡ ቡድኖች ለፖለቲካ ፍጆታቸው እንዲመች ሲሉ በህዝቦች መካከል የሚፈጥሩት ግጭት እንጂ የሀገራችን ህዝቦች እርስ በእርስ የሚጋጩ፣ አንዱን አንዱ ላይ የሚያስነሳ እሴት ያላቸው ህዝቦች አይደሉም ነው ያሉት አቶ ሙስጠፋ፡፡

ፕሬዝዳንቱ በመልዕክታቸው አመራር ላይ ያሉ ግለሰቦች እና ቡድኖች የያዙትን ርዕዮተ-አለም ህዝብ እንዲቀበላቸው ተፅእኖ ለመፍጠር ሲባል የሚወሰዱት እርምጃዎች ህዝብን ከህዝብ የሚያጋጩ እየሆኑ ነው፡፡

በመሆኑም አንድን ርዕዮተ አለም የበላይነት ለማስፈን ሲባል የሰላም እጦት መከሰት የለበትም ብለዋል፡፡

ማንነትን ከፖለቲካ ጋር ሳናያይዝ የቀደመውን አብሮ የመኖር እሴት ልናጎለብት ይገባል ነው ያሉት ፕሬዝዳንቱ፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *