loading
በኢትዮጵያ ዕድገት መደራደር የለም አሉ ጠሚ/ር አብይ አሕመድ፡፡

በኢትዮጵያ ዕድገት መደራደር የለም አሉ ጠሚ/ር አብይ አሕመድ፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትሩ አዲስ በተመረቀው ወለጋ ስቴዲዮም ለነቀምት ከተማ ነዋሪዎች ባደረጉት ንግግር ፤በኢትዮጵያ የተገኘውን ነጻነት ለማምጣት ዋጋ ለከፈሉ በሙሉ ዕውቅና ሰጥተዋል።

በኢትዮጵያ ዕድገት መደራደር የለም ያሉት ጠ/ሚሩ ለነቀምትና ለመላ ኦሮሚያ ክልል ነዋሪዎች የኢትዮጵያንና የክልሉን አንድነት በሰላማዊ መንገድ ለማረጋገጥ ተባብረውና ጠንክረው እንዲሠሩ ጥሪ አቅርበዋል።

ጠ/ሚር አብይ አሕመድና  አቶ ለማ መገርሳ በነቀምት ከተማ ሲደርሱ ነዋሪዎቹ ደማቅ አቀባበል ያደረጉላቸው ሲሆን ጠ/ሚር ዐቢይ አሕመድም አዲሱን ስቴዲየም በጎል መርቀዋል::

80,000 ሰው የማስተናገድ አቅም ያለው የወለጋ ስቴድዮም በከተማዋ ትልቁና ዘመናዊው ስቴዲየምና የወጣት ማዕከል ሲሆን ለከተማዋ ነዋሪዎች የስፖርት ማዘውተሪያና የመዝነኛ ስፍራ በመሆን ያገለግላል።

ለግንባታው እስካሁን 196 ሚሊየን ብር ወጪ የተደረገ ሲሆን፥ ከዚህም ውስጥ 181 ነጥብ 7 ሚሊየን ብሩ በመንግስት የተሸፈነ መሆኑ ተነግሯል።

ስታዲየሙ፥ በዙሪያው ለቢሮና ለንግድ የሚያገለግሉ ሱቆችም አሉት።

ስታዲየሙ በፊፋ መመዘኛ መሰረት ዓለም አቀፍ ደረጃውን ጠብቆ እየተሰራ ሲሆን፥ የእግር ኳስ፣ የቦሊቦልና የቅርጫት ኳስ ሜዳዎች፣ የመሮጫ መምና ሌሎች የመወዳደሪያ ሥፍራዎችን ያካተተ ነው።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *