loading
የዳኛውን እናት የተሳደው ኮስታ የ8 ጨዋታ ቅጣት ተከናንቧል

የአትሌቲኮ ማድሪዱ ስፔናዊ ነውጠኛ አጥቂ ዲዬጎ ኮስታ የስፔናዊውን አርቢትር እናት በመሳደቡ ምክንያት የስምንት ጨዋታዎች ቅጣት ተጥሎበታል፡፡

አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ ከባርሴሎና ጋር በነበረው የካምፕ ኑ ፤ የስፔን ላ ሊጋ መርሀግብር የ2 ለ 0 ሽንፈት ሲያስተናድ፤ ተጫዋቹ በጨዋታው የመጀመሪያው አጋማሽ 27ኛው ደቂቃ ላይ በዕለቱ አርቢትር ሄሱስ ሂል ማንሳኖ ላይ ያልተገባ ባህሪ በማሳየቱ ምክንያት የቀጥታ ቀይ ካርድ አሳይተውት ከሜዳ አሰናብተውታል፡፡

አርቢትሩ በጨዋታው ሪፖርት እንዳካተቱት ኮስታን የቀጥታ ቀይ ካርድ ያሳዩት እናታቸውን በመስደቡ ምክንያት መሆኑን ነው፡፡

የስፔን እግር ኳስ ፌዴሬሽን ባሳለፈው የቅጣት ውሳኔ መሰረት አትሌቲኮ ዴ ማድሪድ በዚህ የውድድር ዓመት የስፔን ላሊጋ የሚቀሩ ጨዋታዎች ላይ ዲዬጎ ኮስታ የማይሳተፍ ይሆናል፡፡

ኮስታ የቅጣቱ ውሳኔ ከተሰማ በኋላ ይግባኝ የመጠየቅ መብት ያለው ሲሆን በቅጣቱ ውስጥ የአራት ጨዋታዎች ቅጣት የተላለፈው ለስድቡ እንዲሁም ቀሪዎቹ አራት ጨዋታዎች ደግሞ የአርቢትሩን እጅ በመያዙ ነው ተብሏል፡፡

                                                                                                                                                                   ቢቢሲ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *