loading
የለንደን ፖሊስ ጁሊያን አሳንጄን በቁጥጥር ስር አዋለው፡፡

የለንደን ፖሊስ ጁሊያን አሳንጄን በቁጥጥር ስር አዋለው፡፡

የዓለማችን ሚስጥራዊ ሰነዶች በእጁ ላይ ናቸው  የሚባልለት የዊኪሊክስ መስራች ጁሊያን አሳንጄ ለሰባት ዓመታ በጥገኝነት ከኖረበት ከኢኳዶር ኢምባሲ በመባረሩ ነው በለንደን ፖሊስ እጅ የገባው፡፡

ኒው ዮርክ ታይምስ እንደዘገበው የለንደን ፖሊስ አሳንጄን የያዘው ከዌስት ሚኒስቴር ማጄስትሬት ፍርድ ቤት የተፃፈለትን የእስር ማዘዣ መሰረት አድርጎ ነው፡፡

የ47 ዓመቱ አሳንጄ የአሜሪካ መንግስት የሀገሬን ጥቅም የሚጎዱ ምስጥራዊ ሰነዶችን በድብቅ መንትፎ አሰራጭቶብኛል ብላ ክስ መስርታበት እንደነበር ይታወቃል፡፡

የስዊዲን መንግስት የአስገደዶ መድፈር ወንጀል ፈፅሟል በሚል ለጥያቄ እንደሚፈልገው ይፋ ማድረጉን ተከትሎ ተላልፎ እንዳይሰጥ በመፍራት ነበር የኢኳዶርን  መንግስት ጥገኝነት የጠየቀው፡፡

የኋላኋላ ግን ኢኳዶር ከአሜሪካ፣ ከእንግሊዝ እና ከሌሎች በአሳንጄ በደል ደርሶብናል ከሚሉ ወዳጆቿ የሚመጣባትን ግፊት መቋቋም ሲያቅታት ለማባረር ተገዳለች፡፡

ኢኳዶር መጀመሪያ አሳንጄን ለንደን በሚገኘው ኢምባሲዋ ካስጠጋችው በኋላ ዜግነት ሰጥታ ዲፕሎማት አድርጋ በመሾም ወደ ሩሲያ ለመላክ ሀሳብ ነበራት፡፡

የማእከላዊ ለንደን ፖሊስ በሰጠው መግለጫ አሳንጄን በእስር ቤት አቆይቶ ከረመረመረ በኋላ በቅርብ ቀን ፍርድ ቤት እንደሚያቀርበው ይፋ አድርጓል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *