loading
ኮካ ኮላ ከምርት ሽያጩ ያሰባሰበውን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች መለገሱን አስታወቀ

ኮካ ኮላ ከምርት ሽያጩ ያሰባሰበውን ከስድስት ሚሊዮን ብር በላይ ገንዘብ ለበጎ አድራጎት ድርጅቶች መለገሱን አስታወቀ

ኩባንያው ይህንን ያስታወቀው በቅርቡ ተካሂዶ የነበረውን የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ ሙዚቃ ፕሮግራም ይፋዊ መዝጊያ ስነስርዓት ባካሄደበት ወቅት ነው።

ሃሙስ ምሽት በስካይ ላይት ሆቴል በተካሄደው በዚሁ ስነስርዓት ላይ እንደተገለጸው ኩባንያው የገንዘብ ድጋፉን ያደረገው የሴቶችና ህጻናት ልማት ድርጅት፣ ታለንት የወጣቶች ማህበር እና የሴቶች የራስ ስራ ፈጠራ ድርጅት ለተባሉ ሶስት በጎ አድራጎት  ድርጅቶች ነው ተብሏል።

ድርጅቶቹ የተመረጡት ኩባንያው በማህበራዊ ሚዲያ በበተነው የአስተያየት መስጫ አሰራር መሰረት ሲሆን አንድ ብር ከአንድ ኮካኮላ በሚል  ዘመቻ የተጀመረውን የገንዘብ ማሰባሰብ ተግባር በህብረተሰቡ ለተመረጡት ድርጅቶች መስጠቱንም አስታውቋል።

የኮካኮላ ኢትዮጵያ ብራንድ ስራ አስጀኪያጅ ትዕግስት ጌጡ ይህንኑ ጉዳይ አስመልክቶ በተዘጋጀው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ እንደተናገሩት የ2019 የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ የሙዚቃ ፕሮግራም የኢትዮጵያን ልዩ ባህላዊ ሙዚቃዎች እና ሙዚቃን ለዓለም ያስተዋወቅንበት መልካም አጋጣሚ ነበር ብለዋል።

ስራ አስኪያጇ እንዳሉት በ2019 የኮክ ስቱዲዮ አፍሪካ ፕሮግራም ላይ 6ሚሊዮን 86 ሺህ 376 ብር ማሰባሰብ የተቻለ ሲሆን ይህንኑ ገንዘብም ሶስቱ በጎ አድራጎት ድርጅቶች አንዲከፋፈሉት ተደርጓል። ይህ ተግባር ኩባንያው ማህበራዊ ሃላፊነቱን የሚወጣት አንዱ መገለጫ ነው ብለዋል ስራ አስኪያጇ።

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *