loading
108 ሰዓሊያን ከ2ሺህ በላይ ስራዎቻቸውን ለሽያጭ ያቀርባሉ

ከሚገኘው ገቢ አቅም የሌላቸውን ታማሚዎችን ለመደገፍ ቃል የተገባበት  የስዕል አውደ ርዕይ እየተዘጋጀ ነው

በአውደርዕዩ 108 ሰዓሊያን ከ2ሺህ በላይ ስራዎቻቸውን ለሽያጭ ያቀርባሉ

ዋትስ አውት ሚድያ ከሄልተን ሆቴል ጋር በጋራ በመሆን The Big Art Sale  የተሰኘ የስዕል አውደ ርዕይ ሚያዚያ 12 ቀን   በሂልተን  ሆቴል  ግቢ ሊያዘጋጅ ማቀዱን  በሰጠው ጋዜጣዊ  መግለጫ አስታውቋል ፡፡

የዚህ አውደ ርዕይ ዋና አላማ  በጥበብ ስራ ላይ  የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን ሰዓሊዎችን መደገፍ ነው ተብሏል።

ከዚህ በተጨማሪም ስዕሎቹ  ተሽጠው  ከሚገኘው ገቢ 20 በመቶው  ደግሞ በጳውሎስ ሆስፒታል ለሚገኙ የህክምና አገልግሎት ወጪ መሸፈን ለማይችሉ ሴት ህሙማን ድጋፍ የሚውል  ነው ተብሏል።

በዕለቱ ቁጥራቸው 108 የሚሆኑ  ወጣት እና አንጋፋ ሰዓሊያን  2ሺ የሚሆኑ  የተለያዩ የስዕል ስራዎቻቸውን  ይዘው ይቀርባሉ ተብሏል።

በዚህ ፕሮግራም ላይ የጥበብ አፍቃሪያን ከሚያደንቋቸው  ሰዓሊያን ጋር  በማገናኝት ዕድል ይፈጠርላቸዋል ነው የተባለው።

የሀገር ውስጥ ሰዓልያን ብቻ የሚሳተፉበት ይህ አውደ ርዕይ ጎብኚዎች  ሰዕሎቹን ከመመልከት ባሻገር የወደዷቸውን የስዕል ስራዎች  በአነስተኛ ዋጋ  መግዛት የሚችሉበት እንደሚሆን የዝግጅቱ አስተባበሪ ወይዘሮ ትዕግስት ደሳለኝ  ለአርትስ  ቲቪ ተናግረዎል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *