Uncategorized

ተመራቂ ሴት ተማሪዎችን ከቀጣሪዎች እና ከስኬታማ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር  የሚያገናኝ አዲስ ፕሮግራም ሊጀመር ነው

ተመራቂ ሴት ተማሪዎችን ከቀጣሪዎች እና ከስኬታማ ሴት ስራ ፈጣሪዎች ጋር  የሚያገናኝ አዲስ ፕሮግራም ሊጀመር ነው

ፕሮግራሙ ለሶስት አመታት የሚቆይ ነው ተብሏል

ኤዩሪያን ሶሊውሽን የተባለ ተቋም ከተለያዩ ድርጅቶች ጋር በመቀናጀት መሪ የተባለ የአመራር እና ማማከር አገልግሎት በነገው ዕለት ይፋ ያደርጋል።

ይህ ፕሮግራም በየዩኒቨርሲቲዎች የሚማሩ የመጨረሻ አመት ተመራቂ ተማሪዎች ከቀጣሪ ተቋማት እና ከሴት ስራ ፈጣሪ ባለሃብቶች ጋር የሚገናኙበትን መንገድ የሚያመቻች ነው ተብሏል።

ኤዩሪያን ሶሊውሽን ለአርትስ ቴሌቪዠን በላከው መግለጫ እንዳብራራው ይህ ፕሮግራም ወጣት ሴቶች የአመራር እውቀታቸው እንዲሰፋ እና የግንኙነት መረባቸው እንዲጠናከር በማድረግ ራሳቸውን የሚገልጡበት እና ክህሎታቸውን የሚያዳብሩበትን መንገድ ይከፍታል ብሏል።

ልምድ እና መረጃ ልውውጥ እውቀትና ክህሎት ኖሯቸው ነገር ግን ተደብቀው ራሳቸውን ማውጣት ያልቻሉ ሴት ወጣቶች በእውቀታቸው የሚያገለግሉበት እና በችሎታቸው የሚጠቀሙበትን እድል ያሰፋል የሚለው ድርጅቱ ፕሮግራሙ ለሚቀጥሉት ሶስት አመታት እንደሚቆይ ጠቁሟል።

የመጀመሪያው የማማከር ፕሮግራም ለሚቀጥሉት ሶስት ወራት የሚካሄድ ሲሆን ሰልጣኞች በአመራር ክህሎት የሚሰጣቸው ስልጠና እና የማማከር አገልግሎት በጎ ፍቃደኛ በሆኑና በተመረጡ  አሰልጣኞች ይካሄዳል ነው የተባለው።

 

 

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button