loading
ጅቡቲ  ለኢትዮጵያ ትምህርት ቤት መገንቢያ ቦታ ሰጠች፡፡

ጅቡቲ  ለኢትዮጵያ ትምህርት ቤት መገንቢያ ቦታ ሰጠች፡፡

ጅቡቲ ለኢትዮጵያ የሰጠችዉ መሬት አራት ሄክታር ስፋት ያለው ሲሆን በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በአገራቸው ካሪኩለም ትምህርታቸውን መከታተል የሚችሉበት ትምህርት ቤት የሚገነባበት ቦታ ነዉ ፡፡

አምባሳደር አብዱልአዚዝ ለኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ትምህርት ቤት እንዲውል ታስቦ በጅቡቲ መንግስት የተሰጠውን መሬት ጎበኝተዋል፡፡
ቀደም ብሎ በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን በኤምባሲው በኩል ትምህርት-ቤት መስሪያ ቦታ እንዲሰጣቸው በጠየቁት መሰረት በጅቡቲው ፕሬዚዳንት ኢስማኤል ዑመር ጊሌ መንግስት ፍቃድ መሬቱ ለኢትጵያ ተሰጥቷል፡፡

ኤምባሲው በጅቡቲ መንግስት ለተደረገው ወንድማማችነትን በተግባር የገለጸ ትብብር በኢትዮጵያ መንግስት ስም ምስጋናውን አቅርቧል፡፡

ትምህርት ቤቱ የሚገነባበት ቦታ እንደ ኢትዮ-ጅቡቲ የባቡር ጣቢያ እና የአፍሪካ አለም አቀፍ ትምህርት ቤት የመሳሰሉ ትላልቅ መሰረተ-ልማቶች ያሉበት ከመሆኑ አንጻር የጅቡቲ መንግስት ለትምህርት ቤቱ መስሪያ ቁልፍ ቦታ መስጠቱን አምባሳደር አብዱልአዚዝ በጉብኝቱ ወቅት ገልጸዋል፡፡

አምባሳደሩ  በጅቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያን ይሄንን ታሪካዊ አጋጣሚ ዕውን ለማድረግ ለትምህርት ቤቱ ግንባታ የተቻላቸውን ሁሉ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *