loading
ሱዳናውያን ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሳሰቡ

ሱዳናውያን ልዩነቶቻቸውን በንግግር እንዲፈቱ ጠ/ሚ አብይ አህመድ አሳሰቡ

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በሱዳን የተደረገውን የመንግስት ለውጥ አስመልክቶ መልዕክታቸውን ያስተላለፉ ሲሆን መላው ሱዳናውያን ያላቸውን ልዩነት በንግግር በመፍታት የጋራ መግባባት ላይ ሊደርሱ እንደሚገባ ጥሪያቸውን አቅርበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልእክታቸዉ አክለዉም ሁሉን አቀፍና ባለ ድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት ማድረግ ይገባል፤ ይህም ዴሞክራሲያዊ፣ ጠንካራና የተዋሃደች ሱዳንን ለመፍጠር የሚደረገውን ጥረት እንደሚያግዝ ጠቁመዋል።

በሚደረጉ የጋራ ውይይቶችና ምክክሮች ልዩነቶች ይጠባሉ ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፥ ልዩነቶች በሃሳብ እንጂ በአስተዳደር ደረጃ ሊኖሩ እንደማይገባም አስገንዝበዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በመልዕክታቸው መላው ሱዳናውያን ድምጻቸውን በሰላማዊ መንገድ በማሰማት በለውጡ ሂደት በሃላፊነት ለተንቀሳቀሱበት መንገድ ያላቸውን አድናቆት ገልጸዋል።

ሂደቱ ጠንካራዋንና ዴሞክራሲያዊቷን ሱዳንን ለመገንባት እንደሚያግዝም በመልእክታቸዉ  አካተዋል።

ከዚህ ሌላም ወታደራዊ የሽግግር ምክር ቤቱ የህዝቡን ፍላጎት ተረድቶ ለውጡን ያካሄደበትን መንገድም አድንቀዋል።

ወቅቱም መላው ሱዳናውያን ለሃገራቸው አንድነት በጋራ ሆነዉ የሚሰሩበት እንደሆነና ለዚህ መሳካት ጎረቤታችሁ ኢትዮጵያ ከሱዳን ጎን ትቆማለች ሲሉ መግለጻቸውን ከጠቅላይ ሚኒስትር ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *