loading
የኢትዮ-ሩሲያ የቢዝነስ ጉባኤ ተካሄደ።

የኢትዮ-ሩሲያ የቢዝነስ ጉባኤ ተካሄደ::

ከ90 በላይ የሩሲያ እና 25 የሚሆኑ የኢትዮጵያ የንግድ ማህበረሰብ አባላት የተሳተፉበት የሁለቱ አገራት የቢዝነስ ጉባኤ በፒተርስበርግ ከተማ ተካሂዷል።

የቢዝነስ ጉባኤው በሩሲያ የኢትዮጵያ ኤምባሲና በፒተርስበርግ ከተማ የንግድና ኢንዱስትሪ ምክር ቤት አስተባበሪነት ነው የተዘጋጀው።

በውይይቱም በሁለቱ አገራት ያሉ የንግድና ኢንቨስትመንት አማራጮች ዙሪያ ምክክር ተደርጓል።

በቱሪዝም ዘርፍ ለተሰማሩ የሩሲያ ኩባንያዎች  ኢትዮጵያ ስላሏት እምቅ የቱሪዝም ሃብት እና የቢዝነስ አማራጮችን  ሞስኮ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ  ቢሮ በኩል  ገለፃ ተደርጎላቸዋል።

ጉባኤው በሁለቱ አገራት የንግድ ማህበረሰቦች መካከል በኢንቨስትመንት፣ በንግድና ቱሪዝም መስኮች የበለጠ ተቀራርቦ ለመስራት መልካም አጋጣሚ የፈጠረ ነው ሲል የውጭ ጉዳይ ቃል አቀባይፅህፈት ቤት ገልጿል ።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *