loading
የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊቢያ የተፈናቃዮች ቁጥር መበራከቱ አአሳስቦኛል አለ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በሊቢያ የተፈናቃዮች ቁጥር መበራከቱ አአሳስቦኛል አለ፡፡

በሊቢያ የሚገኘው የድርጅቱ የሰብዓዊ ጉዳዮች ቢሮ እንዳስታወቀው በተፋላሚ ሀይሎች መካከል በሚደረገው ውጊያ ሳቢያ እስካሁን ከ18 ሺህ በላይ ሰዎች ቀያቸውን ለቀው ተሰደዋል፡፡

ከ3 ሺህ በላይ የሚሆኑ ስደተኞች ደግሞ ውጊያው በሚካሄድበት አቅራቢያ በሚገኙ የማቆያ ማእከሎች መውጫ መግቢያ አጥተው ቀጣዩን እጣ ፋንታቸውን እየተጠባበቁ ይገኛሉ፡፡

የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ዋና ፀሀፊ ቃል አቀባይ ስቴፈን ዱጃሪክን ጠቅሶ ሚድል ኢስት ሞኒተር እንደዘገበው በትፖሊ አቅራቢያ በግጭቱ ምክንያት  የሲቪል ሰዎች መኖሪያ እና መሰረተ ልማቶች እየፈራረሱ ነው፡፡

ድርጅቱ ሁለቱም ተፋላሚ ሀይሎች ለዓለም አቀፍ ህግ ተገዥ እንዲሆኑ እና ተኩስ በማቆም ሲቪል ሰዎችን ከጥቃት እንዲታደጉ ጥሪ አቅርቧል፡፡

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *