loading
ትናንት ምሽት  2 ሰዓት አዋሽ ኬላ ላይ 3 ሺህ 910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ተያዘ

ትናንት ምሽት  2 ሰዓት አዋሽ ኬላ ላይ 3 ሺህ 910 የክላሽ ጥይት በጉምሩክ የፍተሻ ሰራተኞች ተያዘ

የገቢዎች ሚኒስቴር የጦር መሳሪያ እንደ ሌሎች የኮንትሮባንድ ምርቶች ግምታዊ ዋጋ ብቻ የሚወጣለት አይደለም፡፡ የጦር መሳሪ በቁጥጥር ስር ሲውል በዋጋ የማይተመነውን ውድ የሆነውን የሰው ህይወት ከጥፋት መታደግ ነው ብሏል፡፡
መነሻውን ከሀረር መስመር ያደረገ የሰሌዳ ቁጥሩ ኮድ3-47593 ኦሮ የሆነ ሚኒባስ ተሸካርካሪ የአዋሽ መቆጣጠሪያ ጣቢያ ሰራተኞች ባደረጉት ፍተሻ የክላሽ ጥይቱ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

ጥይቶቹ የተያዙት በተሽከርካሪው ላይ በተሰራለት ድብቅ ቦታ ሲሆን የጉምሩክ ተቆጣጣሪዎቹ ያላቸውን ልምድ እና ብቃት በመጠቀም በቁጥጥር ስር አዉለዉታል፡፡
ከትላንት በስቲያ  በተመሳሳይ መስመር አልበርከቴ ኬላ ላይ ብዛቱ 5947 የሆነ የክላሽ ጥይት በቁጥጥር ስር መዋሉ የሚታወስ ነው፡፡

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *