loading
የዩሮፓ ሊግ የመልስ ግጥሚያዎች ዛሬ ምሽት ይደረጋሉ

የ2018/19 የዩሮፓ ሊግ የሩብ ፍፃሜ የመልስ ጨዋታዎች ዛሬ ምሽት ተጠባቂ ጨዋታዎችን ይከናወናሉ፡፡

የእንግሊዙ አርሰናል ወደ ጣሊያን ተጉዞ ሳን ፓውሎ ላይ ከናፖሊ ጋር ይጫወታል፡፡ ባለፈው ሳምንት መድፈኞቹ ኤመሬትስ ላይ 2 ለ 0 ድል ማድረጋቸው የሚታወስ ሲሆን ኔፕልስ ምድር ላይ ፈተና ይጠብቃቸዋል፡፡

አማካዩ ሉካስ ቶሬራ ከቡድኑ ጋር አብሮ እንደተጓዘ ተነግሯል፡፡

በካርሎ አንቼሎቲ የሚመሩት ናፖሊዎች የአማካዩን አማዱ ዲያዋራ እና ስፔናዊውን ተከላካይ ራውል አልቢዮል ግልጋሎት የማያገኙ ይሆናል፡፡

ሌላኛው የእንግሊዝ ክለብ ቼልሲ ስታንፎርድ ብሪጅ ላይ የቼክ ሪፐብሊኩን ስላቪያ ፕራሃን ያስተናግዳል፡፡

ከሊቨርፑል ጋር በነበረው ጨዋታ ጉዳት የገጠመው አንቶኒዮ ሩዲገር ከጨዋታው ውጭ እንደሆነ ተነግሯል፡፡

አማካዩ ኢትሃን አምፓዱ እና ተከላካዩ ማርኮስ አሎንሶ የመሰለፋቸው ነገር አጠራጣሪ ነው ተብሏል፡፡ ሰማያዊዎቹ በመጀመሪያው የፕራግ ጨዋታ 1 ለ 0 ድል ያደረጉ ሲሆን በሜዳቸው ተጨማሪ ጎሎችን ያስቆጥራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በሌሎች ጨዋታዎች ቤንፊካ ወደ ጀርመን አቅንቶ ከአይንትራክት ፍራንክፉርት ጋር ሲጫወት ፤ ቫሌንሲያ ሜስታያ ላይ ቪያሪያልን ያስተናግዳል፡፡

ሁሉም ግጥሚያዎች ምሽት 4፡00 ሲል ሲጀመሩ፤ አርሰናል፣ ቼልሲ፣ ቤንፊካ እና ቫሌንሲያ ግማሽ ፍፃሜውን የመቀላቀል ከፍተኛ ዕድል አላቸው፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *