loading
ላለፉት 8 ዓመታት በኳታር በህክምና የቆየችው ወ/ሮ ሜሮን ወደ አገሯ ተመለሰች፡፡

ላለፉት 8 ዓመታት በኳታር በህክምና የቆየችው ወ/ሮ ሜሮን ወደ አገሯ ተመለሰች፡፡

በኳታር በደረሰባት የጪስ መታፈን አደጋ ጉዳት ላለፉት ስምንት አመታት በሀማድ ሆስፒታል በህክምና ላይ የቆየችው ኢትዮጵያዊት ወ/ሮ ሜሮን መኮንን ትናንት  እኩለ ሌሊት ላይ ወደ አገሯ ተመልሳለች።

ይህ የተቻለውም በቅርቡ ጠቅላይ ሚኒስትር  አብይ አህመድ በኳታር ባደረጉት ጉብኝት ለኳታር መንግስት ባቀረቡት ጥያቄ መሰረት ግለሰቧ በአስቸኳይ ወደ አገሯ እንድትመለስ ስምምነት በመደረሰ ነው።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርና የጤና ሚኒስቴር ተወካዮች በቦሌ አለም አቀፍ የአውሮፕላን ማረፊያ በመገኘት አቀባበል አድርገውላታል።

የኳታር መንግስትም በአገር ቤት ለአንድ አመት መታከሚያ የሚሆናትን ወጪ እና ሙሉ የትራንስፖርት ወጪዋን ይሸፍናል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ከጤና ሚኒስቴር ጋር በመተባበር አስፈላጊውን አቀባበልና ክትትል የሚያደርግላት ይሆናል።

በሆስፒታሉ ቆይታዋ በኳታር የኢፌዴሪ ኤምባሲና በአገሪቱ የአትዮጵያ ኮሚዩኒቲ ክትትልና ድጋፍ ሲያደርጉላት ቆይተዋል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *