loading
ሪክ ማቻር የደህንነት ጉዳዮች መፍትሄ ካላገኙ ወደ ሀገር ቤት አልመለስም አሉ፡፡

ሪክ ማቻር የደህንነት ጉዳዮች መፍትሄ ካላገኙ ወደ ሀገር ቤት አልመለስም አሉ፡፡

የደቡብ ሱዳን ዋነኛ ተቃዋሚ መሪ የሆኑት ሪክ ማቻር አሁን በጁባ ያለው የሰላም እና ፀጥታ ሁኔታ አስጊ በመሆኑ ወደ ሀገራቸው የመመለስ ሀሳብ እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡

ሮይተርስ እንደዘገበው የደቡብ ሱዳን ተፋላሚ ሀይሎች የጥምር መንግስት ለመመስረት በተስማሙት መሰረት ማቻር  ግንቦት ወር  ወደ ጁባ የመመለስ እቅድ ነበራቸው፡፡

የደቡብ ሱዳን መንግስት እና ተቃዋሚዎች ዓመታትን የፈጀ ድርድር ካደረጉ በኋላ ስልጣን ለመጋራት ሲስማሙ ሪክ ማቻር በምክትል ፕሬዝዳንትነት ሊሾሙ ቃል ተገብቶላቸው ነበር፡፡

ይሁን እና አሁን በሀገሪቱ ያለው የደህንነት ሁኔታ አስተማማኝ ስላልሆነ ነገሩ እስኪስተካከል የጋራ መንግስት የመመስረቻ ጊዜው እንዲራዘም ጠይቀዋል፡፡

የሪክ ማቻርን ፓርቲ ወክለው ስለ መንግስት ምስረታው የተናገሩት ስቴፈን ካንግ ኮል የጋራ መንግስት ከመመስረቱ አስቀድሞ ከሁለቱም ወገኖች የተውጣጣ የጦር ሀይል የማደራጀት ስራ እንዳልተሰራም ተናግረዋል፡፡

ይህም ስምምነቱን ተግባራዊ ለማድረግ እንቅፋት ከሚፈጥሩ ጉዳዮች አንዱ መሆኑ እየተነገረ ይገኛል፡፡

የጋራ መንግስት ሲመሰረት ደቡብ ሱዳን በስንት ክልሎች ትዋቀር የሚለውም ገና ስምምነት ላይ ያልተደረሰበት ሌላው ጉዳይ ነው ተብሏል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *