loading
በወ/ሮ ሂሩት የተመራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን ወ/ሮ ሜሮን መኮነንን ጠየቀ

በወ/ሮ ሂሩት የተመራ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የልዑካን ቡድን ወ/ሮ ሜሮን መኮነንን ጠየቀ

በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ወ/ሮ ሂሩት ዘመነ የተመራ የሚኒስቴሩ የልዑካን ቡድን ወ/ሮ ሜሮን መኮነንን በቅዱስ ጴጥሮስ ልዩ ሆስፒታል በመገኘት ጠየቁ፡፡

በዚህም ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር አክሊሉ ሃይለ ሚካኤል፣ የዳያስፖራ እና ቆንስላ ጎዳዮች ቋሚ ተጠሪ ዶ/ር ቦጋለ ቶሎሳ እና የቆንስላ ጉዳዮች ዳ/ጄኔራል አቶ ዮሃንስ ጎፌ ተገኝተዋል።

ወ/ሮ ሜሮን በኳታር በደረሰባት የጪስ መታፈን አደጋ ጉዳት ሳቢያ ላለፉት ስምንት አመታት በሀማድ ሆስፒታል በህክምና ላይ ቀይታ ትናንት ማምሻውን ነው ወደ አገሯ የተመለሰችው።

ወ/ሮ ሂሩት በዚሁ ወቅት እንዳሉት ታማሚዋ በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥያቄ ወደ አገሯ መመለስ በመቻሏ የተሰማቸውን ደስታ ገልጸዋል።

የውጭ ጉዳይ ሚኒቴር በቀጣይም ከሚመለከታቸው ተቋማት ጋር በመሆን ክትትልና ድጋፍ ማድረጉን እንደሚቀጥል ተናግረዋል።

ዶ/ር አክሊሉ ኃይለሚካኤል በበኩላቸው ሆስፒታሉ ዜጎች በአገራቸው እንዲታከሙ ማስቻሉ ትልቅ ስኬት መሆኑን ገልጸው በዘርፉ ከሚሰሩ የውጭ አገራት የህክምና ተቋማት ጋር ትስስር እንዲፈጥር ውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ይሰራል ብለዋል።

የቅዱስ ጴጥሮስ ልዩ ሆስፒታል ዋና ስራ አስፈጻሚ ዶ/ር ታምሩ አሰፋ እንዳሉት ወ/ሮ ሜሮን በተሻለ ጤንነት ላይ እንደምትገኝ ገልጸው ሆስፒታሉ አስፈላጊውን እንክብካቤ እንደሚያደርግላት ተናግረዋል።

የወ/ሮ ሜሮን መኮነን አስታማሚና ልጅ ወጣት ቢኒያም ይልማ ለእናቱ ለተደረገላት ድጋፍ ጠቅላይ ሚኒስትር ክቡር ዶ/ር አብይ አህመድን፣ በኳታር የኢትዮጵያ ኤምባሲ ዲፕሎማቶች፣ ሰራተኞችና በአገሪቱ የሚኖሩ የኢትዮጵያ ኮሚዩኒቲ እንዲሁም የኳታር መንግስትን አመስግኗል።

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *