loading
ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ በዛሬው ዕለት ለአራት ከፍተኛ አመራሮች ሹመት ሰጡ።

በዚሁ መሰረት  ቀድሞ የኦዲፓ ማዕከላዊ ጽህፈት ቤት ሃላፊ የነበሩትን ዶ/ር አለሙ ስሜን የብረታ ብረትና ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን ምክትል ዋና ዳይሬክተር

ቀድሞ የከተማ ልማት እና ኮንስትራክሽ ሚኒስትር የነበሩትን አቶ ጃንጥራር አባይን የጠቅላይ ሚኒስትሩ የመሰረተ ልማትና የከተማ ልማት አማካሪ ሚኒስትር

ቀድሞ የኦሮሚያ ክልላዊ መንግስት ምክትል ርዕሰመስተዳድር የነበሩት ወ/ሮ ጠይባ ሀሰን በሚኒስትር ማዕረግ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የማህበራዊ ዘርፍ አማካሪ በመሆን ከሚያዚያ 9፣ 2011 ጀምሮ በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዐቢይ አህመድ መሾማቸው የጠቅላይ ሚኒስትሩ ጽሕፈት ቤት  አስታውቋል።

ከዚሁ ጋር በተያያዘ አቶ ገዛሃኝ አባተ ከሚያዚያ 4 ቀን 2011 ጀምሮ የኢትዮጵያ የሆቴልና ቱሪዝም ሥራ ማሰልጠኛ ማዕከል ምክትል ዋና ዳይሬክተር ሆነው ተሹመዋል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *