loading
ጋህነን የትጥቅ ትግሉን ትቶ ወደሃገሩ ገባ

በኤርትራ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ የነበረው የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ በሰላማዊ መንገድ በኢትዮጵያ ፖለቲካ ተሳታፊ ለመሆን ወደ ሀገሩ ገባ።

የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ (ጋህነን) መቀመጫውን ኤርትራ በማድርግ የትጥቅ ትግል ሲያካሂድ ዓመታትን አስቆጥሯል።

የንቅናቄው አባላትና አመራሮች ጋምቤላ አውሮፕላን ማረፊያ ሲደርሱም የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉን ጨምሮ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮችና ደጋፊዎቻቸው አቀባበል አድርገውላቸዋል።

የንቅናቄው ሊቀመንበር አቶ ኡኬሎ ኡኪዲ እንደተናገሩት ቀደምሲል ሰላማዊ የፖለቲካ ትግል ለማካሄድ ምቹ ሁኔታ ባለመኖሩ ንቅናቄው የትጥቅ ትግልን አማራጭ በማድረግ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም ገልጸው አሁን ግን የቀረበለትን የሰላም ጥሪ በመቀበል በሀገር ውስጥ የተፈጠረውን መልካም ሁኔታ ተጠቅሞ ሰላማዊ ትግሉን ለመቀጠል ወደ ሀገር ቤት ገብቷል ብለዋል።

የንቅናቄው አመራርና አባላት ወደ ጋምቤላ ሲገቡ የክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ላደረጉላቸው አቀባበልም ምስጋናቸውን አቅርበዋል፡፡

በአቀባበል ስነ-ስርዓቱ ላይ የተገኙት የክልሉ ርዕሰ መስተዳድር አቶ ኡሞድ ኡጁሉ በበኩላቸው፥ የጋምቤላ ህዝቦች ነፃነት ንቅናቄ የትጥቅ ትግሉን በመተው በሰላማዊ መንገድ ለመታገል መወሰኑ የሚበረታታ ነው ብለዋል።

የክልሉ መሪ ድርጅት ጋህአዴንም ሆነ ጋህነን እና ሌሎች ተፎካካሪ ፓርቲዎች የሃሳብ ልዩነቶች ቢኖሩም እንኳን ልዩነታቸውን በማጥበብ ለክልሉ ሁለንተናዊ ልማት መስራት ይገባቸዋል ነው ያሉት።

ለዚህም የክልሉ መሪ ድርጅትና መንግስት ከህዝቡ ጋር በመሆን ወደ ክልሉ ለገቡ የፖለቲካ ፓርቲዎች አንድ በሚያደርጉ ጉዳዮች በጋራ ለመስራትና ለውጡን ለማስቀጠል ዝግጁ እንደሆነ አስታውቀዋል ይላል ከክልሉ መንግስት  ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *