loading
ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ የሚያስችል የ264 ሚሊየን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራረሙ

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ የሚያስችል የ264 ሚሊየን ዶላር ብድር ስምምነት ተፈራረሙ ።

ኢትዮጵያና ደቡብ ኮሪያ የ264 ሚሊየን ዶላር ቀላል ብድር ማቅረብ የሚያስችል የማዕቀፍ ስምምነት ተፈራረሙ።

ስምምነቱን የደቡብ ኮሪያ ኤክስፖርትና ኢምፖርት ባንክ እና የገንዘብ ሚኒስቴር የተፈራረሙ ሲሆን፤ በኢትዮጵያ ውስጥ ለሚከናወኑ የልማት ፕሮክቶች የሚውል ነው ተብሏል።

የመጀመሪያው የ170 ሚሊየን ዶላር የብድር ስምምነት በደቡብ ኢትዮጵያ ለሚገኘው የብሔራዊ የኤሌክትሪክ ኃይል ፍሰትና የኤሌክትሪክ ማስተላለፊያ ፕሮጀክት የሚውል መሆኑ በስምምነቱ ወቅት ተገልጿል።

በዚህም በኢትዮጵያ በሰሜን ምዕራብ ለሚገኙ የሀገሪቱ ክፍሎችና እና ለኦሞ ስኳር ፋብሪካ ከፍተኛ የኤሌክትሪክ ሀይል ለማቅረብ ያስችላል ተብሏል፡

በተጨማሪም ለአርባምንጭ ኢንዱስትሪያል ፓርክ ግንባታም ይውላል መባሉን ከገንዘብ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።

ሁለተኛው የ94 ሚሊየን ዶላር የቀላል ብድር ስምምነት ደግሞ በሀገሪቱ ውስጥ ለሚሰሩ የመስኖ ልማትና የገጠር ልማት ፕሮጀክቶች እንደሚውል ተጠቅሷል፡፡

በዚህም አርሶ አደሩ የግብርና ምርቱን እንዲያሳድግና ገቢው እንዲጨምር ያደርጋል ተብሏል።

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *