AfricaPolitics

አልጀሪያ 5 ቢሊዮነሮችን አሰረች፡፡

እነዚህ ቱጃሮች እስር ቤት የገቡት የሀገሪቱ ጦር ሀይሎች አዛዥ የቀደመው አስተዳደር ጋር ግንኙነት የነበራቸው ሙሰኞችን በቁጥጥር ስር አውለን ለፍርድ እናቀርባለን የሚል መግለጫ መስጠታቸውን ተከትሎ ነው፡፡

አልጀዚራ እንደዘገበው ኢሳድ ረብራብ ሴቪታ የተባለው በአልጀሪያ ትልቁ  የአግሮ ፐሮሰሲንግ ዘርፍ የተሰማራ የግል ኩባንያ መስራች እና ዋና ስራ አስፈፃሚ ኢሳድ ረብራብ እና ሌሎች አራት ወንድማማቾች በሙስና ተጠርጥረው ታስረዋል፡፡

በተለይ አራቱ ግለሰቦች ከቀድሞው ፕሬዝዳንት የአብደላዚዝ ቡተፍሊካ የቅርብ ሰዎች ናቸው ተብሎ ይታመናል፡፡

የአልጀሪያ ፍርድ ቤት የቀድሞውን ጠቅላይ ሚኒስትር አህመድ ኦያህያን እና የአሁኑን የፋይናንስ ሚነስትር ሞሀመድ ሉካልን ጠርቶ በጉዳዩ ዙሪያ አነጋግሯቸዋል ተብሏል፡፡

በሚያዚያ ወር መጀመሪያ ላይ አሊ ሀዳድ የተባሉ ባለ ሀብት ወደ ጎረቤት ቱኒዚያ በርካታ ገንዘብ ይዘው ለማምለጥ ሲሞክሩ መያዛቸው ይታዋሳል፡፡

መንገሻ ዓለሙ

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button