loading
የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው

የምግብ ዘይት በማምረት የሚታወቀው ጎልደን አፍሪካ የተባለ የማሌዥያ ኩባንያ በኢትዮጵያ ስራ ሊጀምር ነው

 

ኩባንያው በኢትዮጵያ የምግብ ዘይት ምርት ላይ ለመሰማራት ፍላጎት ማሳየቱን ተከትሎ የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስትር ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገብረእግዚአብሄር ለኩባንያው ሀላፊዎች በዘርፉ ባለው የኢንቬስትመንት እድል ዙሪያ ማብራሪያ ሰጥተዋል ።

በኢትዮጵያ ያለው የምግብ ዘይት ፍላጎት ከፍተኛ ቢሆንም 90 በመቶ የሚደርሰው ምርት ከውጭ አገራት በግዢ የሚገባ መሆኑን የተናገሩት ወ/ሮ ፈትለወርቅ በከተማም ሆነ በገጠር የህዝቡ የኑሮ ደረጃ በተሻሻለ ቁጥር የሸማቹ የምግብ ዘይት ፍላጎትና ምርጫ ከፍ ስለሚል በዘርፉ መሰማራት አዋጭ ነው ብለዋል።

ከውጭ አገራት የሚገቡ ምርቶችን በአገር ውስጥ ለሚያመርቱ ኢንቬስተሮች አገሪቱ ጠንካራ የታሪፍ ጥበቃ እንደምታደርግ ሚንስትሯ አብራርተዋል፡፡

የኩባንያው ዋና ስራ አስፈፃሚ ፎድ ሀይል በበኩላቸው በኢትዮጵያ ምቹ የኢንቬስትመንት እድሎች በመኖራቸው በምግብ ዘይት ዘርፍ መዋዕለ ንዋያችንን በስራ ላይ ለማዋል  ፍላጎት አለን ብለዋል።

ኩባንያው በሁለት ዓመት ጊዜ ውስጥ በኢትዮጵያ የምርት ስራውን እንደሚጀምርና ለ1 ሺህ 500 ዜጎች የስራ እድል እንደሚፈጥር በውይይቱ ላይ ተገልጿል።

መረጃውን ከንግድና ኢንዱስትሪ ሚኒስቴር አግኝተነዋል።

 

 

 

 

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *