loading
የማንቹሪያን ደርቢ ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬ ምሽት ይደረጋል

ምሽት 3፡45 ላይ ወልቨርሃምፕተን ዋንደረርስ በሞሊኒክስ ስታዲየም የሰሜን ለንደኑን አርሰናል ያስተናግዳል፡፡ መድፈኞቹ የቀጣይ ዓመት የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ የሚያሳስባቸው በመሆኑ በምሽቱ ግጥሚያ ድል ማድረግ ይጠበቅባቸዋል፡፡ ነገር ግን በኑኖ እስፕሪቶ ሳንቶ የሚመሩት ወልቭሶች ካላቸው የጨዋታ እንቅስቃሴ አንፃር ለአንግዳው የኡናይ ኢመሪ ቡድን ውጋት ሊሆን እንደሚችል ይጠበቃል፡፡

ባለሜዳዎቹ ሙሉ ቡድናቸውን ይዘው ወደ ሜዳ ይገባሉ ተብሏል፤ አርሰናል አሮን ራምሴ እና ዴኒስ ሱዋሬዝን በጉዳት ምክንያት የማያሰልፍ ይሆናል፡፡ በግራኒት ዣካ የመሰለፍ ጉዳይ ግን እርግጠኛ መሆን አልተቻለም፡፡ ሶቅራቲስ ፓፓስታቶፖሎስ ከሁለት ጨዋታዎች ቅጣት መልስ ከምሽቱ ፍልሚያ ይኖራል፡፡ 

ሌላኛው የማንቹሪያን ደርቢ ተጠባቂ ጨዋታ ዛሬ ምሽት 4፡00 ሲል በግዙፉ ኦልድ ትራፎርድ ስታዲየም በሁለቱ የማንችስተር ከተማ ተቀናቃኝ ክለቦች ዩናይትድ እና ሲቲ መካከል ይካሄዳል፡፡

ጨዋታው ከደርቢ ስሜቱ በተጨማሪ ለሻምፒዮንነት እና የቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ፍንጭ የሚሰጥ በመሆኑ በትልቁ ይጠበቃል፡፡

ባለሜዳዎቹ ቀያይ ሰይጣኖች በቀጣይ ዓመት የአውሮፓ ቻምፒዮንስ ሊግ ተሳትፎ ለማግኘት ከቶተንሃም፣ ቼልሲ እና አርሰናል ጋር እየተፎካከረ ሲሆን ውሃ ሰማያዊዎቹ ደግሞ የሊጉን ዋንጫ ወደ ኢቲሃድ ለመውሰድ ከሊቨርፑል ጋር ትንቅንቅ ውስጥ ናቸው፡፡

ከቻምፒዮንስ ሊጉ ስንብት በኋላ የአራትዮሽ ዋንጫ ጉዞው የተገታበት የፔፕ ጓርዲዮላው ቡድን ደጋፊዎቻቸውን ለመካስ ሲሉ የፕሪምየር ሊጉን ዋንጫ በማሸነፍ ለመካስ ተዘጋጅተዋል፡፡

የአሰልጣኝ ኦሌ ጉናር ሶልሻዬር ቡድን በተለያዩ ውድድሮች ሽንፈት ማስተናገዳቸውንና ወጥ አቋም አለማስመዝገባቸውን ተከትሎ ተጫዋቾቻቸውን እየኮነኑ ነው፡፡

በምሽቱ ግጥሚያ አንደር ሄሬራ ከጉዳት መልስ ሊኖር እንደሚችል ሲነገር ሉክ ሻው ደግሞ ከቅጣት የሚመለስ ይሆናል፡፡

የሲቲው ሁነኛ አማካይ ኬቨን ዴ ብሯይኔ የጡንቻ ላይ ጉዳት ስላለበት የደርቢው ፍልሚያ የሚያልፈው ይሆናል፡፡ ግብ ጠባቂው ክላውዲዮ ብራቮ በጉዳት የማይኖር ሌላኛው ተጫዋች ነው፡፡ ሌላው የቡድኑ ስብስብ በሙሉ ጤንነት ውስጥ ይገኛል ተብሏል፡፡

ፔፕ ጓርዲዮላ የዋንጫ ክብራችንን ለማስጠበቅ አራት ጨዋታዎችን በድል መወጣት አለብን ብሏል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *