EthiopiaSportSports

በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመቐለ የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል

የሊጉ የ22ኛ ሳምንት ጨዋታዎች ዛሬ በክልል እና አዲስ አበባ ስታዲየሞች ይከናወናሉ፡፡ ከአንድ ጨዋታ በስተቀር ሌሎች ግጥሚያዎች ክልል ላይ ይደረጋሉ፡፡ ክልል ላይ የሚከወኑት እነዚህ ጨዋታዎች በተመሳሳይ 9፡00 ይደረጋሉ፡፡

አዳማ ከተማ በአዳማ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ላይ በአሰልጣኝ ገዛህኝ ከተማ የሚሰለጥነውን ኢትዮጵያ ቡና የሚገጥም ይሆናል፡፡

ባህር ዳር ከነማ በግዙፉ የከተማው ስታዲየም ከሊጉ ላለመውረድ እየተፍጨረጨረ የሚገኘውን ደቡብ ፖሊስ ያስተናግዳል፡፡

ጎንደር ላይ ደግሞ ፋሲል ከነማ በፋሲለደስ ስታዲየም ከድሬዳዋ ጋር ብርቱ ፉክክር የታከለበት ጨዋታ ያደርጋል፡፡

 መከላከያ ወደ ደቡብ ኢትዮጵያ ተጉዞ ሶዶ ላይ ከወላይታ ድቻ ጋር ይጫወታል፡፡ ሀዋሳ ከተማ ወደ ትግራይ ተጉዞ ሽረ ላይ ወረጅ ቀጠና ውስጥ የሚገኘውን ስሑል ሽረን ይጎበኛል፡፡

መቐለ ላይ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ በትግራይ ስታዲየም ከደደቢት ጋር የደርቢ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ፡፡

ጅማ አባ ጅፋር ጅማ ላይ ከሲዳማ ቡና ጋር ይፋለማል፡፡

የሳምንቱ መርሀግብር ተጠባቂ ጨዋታ ደግሞ ቅዱስ ጊዮርጊስ አዲስ አበባ ስታዲየም ላይ የሊጉን መሪ መቐለ 70 እንደርታ 11፡00 ሲል ይገጥማል፡፡

መቐለ በ45 ነጥብ ሊጉን አሁንም በመሪነት ሲይዝ፣ ፋሲል እና ሲዳማ በተመሳሳይ 37 ነጥብ በግብ ክፍያ ተበላልጠው ሁለተኛ እና ሶስተኛ ደረጃ ሲገኙ፤ ጊዮርጊስ እና ጅማ አባ ጅፋር በተመሳሳይ 34 ነጥብ እንዲሁ በግብ ክፍያ ተበላልጠው አራተኛ እና አምስተኛ ደረጃን ይዘዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button