AfricaEthiopia

በጋራ የድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለዉጦችን የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ በመሆናቸዉ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢትዮጵያ አሳሰበች::

አዲስ አበባ፣ታህሳስ 15፣ 2013 በጋራ የድንበር አካባቢ በሱዳን በኩል የተደረጉ አዳዲስ ለዉጦችን የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ በመሆናቸዉ በአስቸኳይ እንዲቆሙ ኢትዮጵያ አሳሰበች:: የጠቅላይ ሚኒስቴር ፕሬስ ሰክሬተርያት ጽ/ቤት ለአርትስ በላከዉ መረጃ እንዳስታወቀዉ፤ ሱዳን ከጥቅምት ወር መጨረሻ ጀምሮ ድንበር አካባቢ የቀደሙ ስምምነቶችን የሚጥሱ ፤እና መሬት ላይ ያለዉን እዉነታ የሚለዉጡ እንቅስቃሴዎችን እያደረገች እንደሆነና እንቅስቃሴዉ በአስቸኳይ
እንደቆምና ወደቀደመዉ ቦታ እንዲመለስ የኢትዮጵያ መንግስት አሳስቧል፡፡

ሁለተኛዉ የኢትዮጵያ ሱዳን ድንበር ጉዳዮች የከፍተኛ ደረጃ የፖለቲካ ዉይይት በካርቱም ሱዳን ለሁለት ቀን በተካሄደበት ወቅት ፤ሁለቱ ሀገሮች የጋራ ድንበርን በተመለከተ ያሉ ማናቸዉም ዓይነትልነቶች ሁሉንም በሚያስማማ መንገድ በዉይይት ስለመፍታት እና የወደፊት አቅጣጫ ምን ይሁን በሚለዉ ዙሪያ መክረዋል፡፡

በኢትዮጵያ በኩል የድንበሩን ጉዳይ ሰላማዊ በሆነ መልኩ ከቀደሙ ስምምነቶች ጋር በተጣጣመ መንገድ ከድንበሩ ጋር በተያያዘ የተቋቋሙና ስራቸዉን ያላጠናቀቁ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን ስራቸዉን እንደገና እንዲጀምሩ በማድረግ መፍታት እንዳለበት ተገልጿል፡፡ በዉይይቱ በምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር እና የዉጭ ጉዳይ ሚኒስትር አቶ ደመቀ መኮነን የተመራ ልኡክ የተሳተፉ ሲሆን በሱዳን ደግሞ በጠቅላይ ሚኒስትር አብደላ ሐምዶክ የተመራ ልኡክ ተሳትፏል፡፡
ዉይይቱም በቀጣይ ለሁለቱም በሚመች ግዜ በአዲስ አበባ ለማድረግ ተስማምተዋል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button