EthiopiaUncategorized

በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለዳያስፖራዎች እስከ 30 በመቶ ቅናሽ አደረጉ::

አዲስ አበባ፣ ታህሳስ 07፣ 2014 በአዲስ አበባ የሚገኙ ባለ ኮከብ ሆቴሎች ለገናና ጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ ለሚመጡ አንድ ሚሊዮን ዲያስፖራዎች እስከ ሰላሳ በመቶ የሚደርስ ልዩ ቅናሽ ማድረጋቸውን የአዲስ አበባ ሆቴል ባለቤቶች ማህበር ገለጸ። የአዲስ አበባ የሆቴል ባለቤቶች ማህበር ሥራ አስኪያጅ አቶ አምሀ በቀለ ለኢትዮጵያ ፕሬስ ድርጅት
እንደገለጹት፤ በመዲናዋ የሚገኙ ባለኮከብ ሆቴሎች ለገናና ለጥምቀት በዓላት ወደ ኢትዮጵያ የሚመጡ አንድ ሚሊዮን ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያንን ተቀብለው በልዩ ቅናሽ ለማስተናገድ ዝግጅት አድርገዋል።


የሆቴል ባለቤቶች ማህበር አባል ከሆኑ ከ175 በላይ የሆቴል አመራሮች ጋር በተደረገ ውይይት ልዩ ቅናሽና መስተንግዶውን በተመለከተ ገለጻ ተደርጓል። ‹‹የአገር ልጅ›› የተሰኘ ልዩ የዋጋ ቅናሽ ያለው አገርኛ ፓኬጅ ተዘጋጅቷል። የእንግዶችን ፍላጎቶች ሊያሟሉ የሚችሉ ሌሎች አገልግሎቶችን መስጠት እንዲቻልም ማህበሩ የተለያዩ አሰራሮችን ዘርግቷል፡፡

Related Articles

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Back to top button