loading
ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች::

አዲስ አበባ፣ ሚያዝያ 18፣ 2014 ሩሲያ ዩክሬን ላይ የኒውክሌር ግጭት ሊቀሰቀስ እንደሚችል አስጠነቀቀች:: ሞስኮ ባወጣችው መግለጫ ኔቶ ለዩክሬን የጦር መሳሪያ በማቀበል የእጅ አዙር ጦርነት ከፍቶብኛል ስትል ወቀሳ ሰንዝራለች፡፡ የሩሲያው የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሰርጌ ላቨሮቭ ከአንድ የሀገሪቱ ቴሌቪዥን ጣቢያ ጋር ባደረጉት ቃለ መጠይቅ መላው ዓለም ይህን ጉዳይ አቅልሎ መመልከት የለበትም ሲሉ አስጠንቅቀዋል፡፡


የላቭሮቭ ቃለ መጠይቅ የተሰራጨው የአሜሪካ የወጭ ጉዳይና የመከላከያ ሚኒስትሮች ዩክሬንን ከጎበኙ ከሰዓታት በኋላ መሆኑን አልጀዚራ በዘገባው አስነብቧል፡፡
ሁለቱ ባለስልጣናት በጉበኝታቸው ወቅት ኬቭን በወታደራዊ ሃይል የማጠናከር ዓላማ እንዳላቸው መግለጻቸው ተሰምቷል፡፡ በተለይ የመከላከያ ሚኒስትሩ ሊዮይድ አውስቲን ሞስኮ ተዳክማ ማየት የዋሽንግተን ፍላጎት መሆኑን የሚገልጽ ንግግር ማድረጋቸው ከሩሲያ በኩል ቁጣን ቀሰቅሷል ነው የተባለው፡፡


ሶስተኛው የዓለም ጦርነት እንዳይቀሰቀስ መወሰድ ስላለበት ጠቃሚ እርምጃ የተጠየቁት ላቭሮቭ በበኩላቸው እኛ ትልቁ እሴታችን ምንጊዜም ጉዳትን መቀነስ ነው፤ ኔቶና አጋሮቹ ግን ስጋትን ማባባስ ነው ብለዋል፡፡ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ አክለውም አሜሪካ በንግግር ከመተማመን ይልቅ በተናጠል የዲፕሎማሲ ግንኙነቶችን በማቋረጥ በውስጥ ጉዳያችን ጣልቃ መግባትን መርጣለች ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ ምራባዊያን የጸረ ታንክ ሚሳኤሎች፣ የተራቀቁ ሰው አልባ አውሮፕላኖችንና ብረት ለበስ ተሸከርካሪዎችን ለዩክሬን ማቅረባቸውን ካልተው ጦርነቱ በፍጥነት አይቋጭም፤ የተባለው ስጋትም ይቀጥላል ብለዋል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *