loading
በስምንት ቀናት ውስጥ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከአዘዋዋሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ።

አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 2፣ 2014 በስምንት ቀናት ውስጥ ከ127 ሚሊዮን ብር በላይ የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎችን ከአዘዋዋሪዎች ጋር በቁጥጥር ስር ማዋሉን የጉምሩክ ኮሚሽን ገለጸ። ኮሚሽኑ ከሐምሌ 21 ቀን እስከ 28 2014 ዓ.ም ባደረገው ዘመቻ ነው የኮንትሮባንድ እቃዎችን ሲያዘዋውሩ የተገኙ 14 ሰዎችን በቁጥጥር ስር ያዋለው፡፡


በተጠቀሱት ቀናት 118 ነጥብ 5 ሚሊዮን የገቢ ኮንትሮባንድ እቃዎች እና ከ9 ሚሊዮን ብር በላይ የወጭ በድምሩ 127 ነጥብ 6 ሚሊዮን ብር የሚያወጡ የኮንትሮባንድ እቃዎች በተለያዩ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች ተይዘዋል፡፡የገቢ ኮንትሮባንድን በመቆጣጠር ረገድ ቀዳሚውን ስፍራ የሚይዙት አቃቂ ቃሊቲ፣ አዲስ አበባ
ኤርፖርትና ምያሌ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች መሆናቸውን ከኮሚሽኑ ያገኘነው መረጃ ያሳያል፡፡


በነዚህ ቅርንጫፍ ጽህፈት ቤቶች የተያዙት የኮንትሮባንድ እቃዎች ከ60 ሚሊዮን ብር በላይ ግምታዊ ዋጋ እንዳላላቸው ነው ኮሚሽኑ የገለጸው፡፡
በቁጥጥር ስር ከዋሉት የኮንትሮባንድ እቃዎች መካከል ተሽከርካሪን ጨምሮ አልባሳት፣ ነዳጅ፣ የቁም እንስሳት፣ መድሀኒትና ቡና ይገኙበታል፡፡
የኮንትሮባንድ ዕቃዎቹ የጉምሩክ ኮሚሽን ሰራተኞች፣ የፌደራል ፖሊስ፣ የክልል ፖሊስ አባላትና ህብረተሰቡ ባደረጉት የጋራ ጥረት በፍተሻ፣ በበረራና በጥቆማ የተያዙ ናቸው ተብሏል። የኮንትሮባንድ እና ህገወጥ ንግድ የአፈጻጸም ስልቱ ተለዋዋጭ በመሆኑ ድርጊቱን ለመግታትና በሀገር ኢኮኖሚ ላይ የሚያሳድረውን ተጽእኖ ለመከላከል ሁሉም አካላት የበኩላቸውን ድርሻ እንዲወጡ የጉምሩክ ኮሚሽን ጥሪ አቅርቧል፡፡

Write a Reply or Comment

Your email address will not be published. Required fields are marked *